Saturday, May 16, 2020

መልክአ ሥዕል


1. ምንተኑ አዓሥየኪ ዕሤተ፣
በእንተ ኵሉ ዘገበርኪ ሊተ፣
ማርያም ሠናይት ዘታፈቅሪ ምሕረተ፣
ሶበሰ ተትዓቀቢ ዘዚአየ ኃጢአተ፣
እምኢሐዮኩ አሐተ ሰዓተ።
2. በሰላመ ገብርኤል መልአክ ኦ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ፣
ድንግል በኅሊናኪ ወድንግል በሥጋኪ፣
እመ እግዚአብሔር ጸባዖት ሰላም ለኪ፣
ቡርክት አንቲ እምአንስት ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ፣
ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ።
3. ኦ ርኅሩኀነ ልቡና አፍቅሮተ ሰብእ ልማድክሙ፣
በጥቡዕ ልብ ንስእለክሙ፣
ሥሉስ ቅዱስ ምሕረተክሙ አዝንሙ፣
ክሣደ ፀርነ በሰይፍክሙ ግዝሙ፣
ወዲበ ርእስነ ዓዲ እዴክሙ ሢሙ።
4. ኦ ርኅርኅተ ኅሊና አፍቅሮተ ሰብእ ልማዳ፣
ሰአሊተ ምሕረት ይእቲ ማርያም ሐፁረ መስቀል ዘየዓውዳ፣
ንትቀበላ ንዑ ለወለተ ዳዊት ዘይሁዳ፣
መጽአት ነዋ ኅቡረ ምስለ ወልዳ፣
ናንፈርዕፅ ቅድመ ሥዕላ እንዘ ንሁብ ጋዳ፣
ለለጌሠሙ ትመስል እንግዳ።
5. ኦ ርኅርኅተ ኅሊና ዘሕገ ልማዳ ምሕረት፣
ለኵሉ ፍጥረት፣
ንሳለማ ንዑ ለሥዕለ ማርያም ቡርክት፣
ወለሥዕለ ወልዳ ጸባዖት ወለሥዕለ ጊዮርጊስ ሰማዕት፣
ሥዕለ ሚካኤል ወገብርኤል ወሩፋኤል ዘራማ ኃይላት።
6. ኦ ርኅርኅተ ኅሊና ፍቅርኪ ያነድድ አማዑተ፣
ከዊኖ እሳተ፣
ንጽሐ ድንግልናኪሰ እንተ ኢያእመረ ርስሐተ፣
ማርያም ግበሪ ሠናያተ ኵሎ ዕለተ፣
ሞትሰ ድልው ሊተ፣
ባሕቱ ለንሥሓ ጽንሕኒ ንስቲተ።
7. ኦ ርኅርኅተ ኅሊና ለእግዚአብሔር አስከሬኑ፣
እንተ ኢያውዓየኪ እሳተ ርስኑ፣
መሐርኒ ድንግል ወተሣሃልኒ በበዘመኑ፣
ለእመ መሐርክኒ እግዝእትየ ዘይኴንነኒ መኑ፣
ኰናኔ ሥጋ ወነፍስ ወልድኪ አኮኑ።
8. ኦ ርኅርኅተ ኅሊና እንተ ኤልያስ ደመና፣
ወለተ ኢያቄም ወሐና፣
ማርያም ዑጽፍት ወኁብርት በቅድስና፣
ሶበ ነጸረኪ ሙሴ በሲና፣
ኅትምት በድንግልና አልባቲ ሙስና።
9. ተአምርኪ ብዙኅ ዘአልቦ ፍጻሜ፣
በርኅበ ዓለም ሰፈነ አምሳለ ደመና ወጊሜ፣
ማርያም ድንግል ደብተራ ጳውሎስ ዘብሔረ ሮሜ፣
ተማሕፀንኩ በሕፃንኪ ዘሐዘለቶ ሰሎሜ፣
እንበለ ንሥሓ ኢይሙት ወስክኒ እድሜ።
10. ቅድመ ሥዕልኪ እሰግድ ወአስተበርክ ክሡተ፣
ቅድመ ማኅበራንኪ እሉ እንዘ እቀውም ድርገተ፣
ፈጻሚተ መፍቅድ ማርያም እስእለኪ ስእለተ፣
ጸግውኒ እግዝእትየ ለዓለመ ዓለም ሕይወተ፣
እምእደ እኩያን አፅራርየ አድኅንኒ ሊተ።
11.ቅድመ ሥዕልኪ እሰግድ ወለሥዕለ ወልድኪ እገኒ፣
ማርያም ድንግል ማርያም እመ አዶኒ፣
ማዕበለ ጌጋይ ጽኑዕ ሶበ ለአስጥሞ በጽሐኒ፣
ሐመርየኒ ማዕዶትየኒ ሃይማኖትየኒ፣
ማርያም ዘእንበሌኪ አልብየ ምንትኒ።
12. ሰላም ለሥዕልኪ ዘይኤድም ለንጻሬ፣
ዓዲ ሰላም ወለሥዕለ ወልድኪ በኁባሬ፣
አክሊለ ሢመቱ ለጴጥሮስ ማርያም እንተ ትፀድሊ እምወራውሬ፣
ለተአምርኪ ባቊዕ ሶበ ናቄርብ ዝማሬ ፣
ክድንነ ለአግብርትኪ ሣህለኪ ጶደሬ።
13. ሰላም ለሥዕልኪ መዓዛ ቅዳሴ ዘቦቱ፣
ወለሥዕለ ወልድኪ ሰላም ዘያስተፌሥሕ ስነ ርእየቱ፣
ለሐዋርያ እንድርያስ ቀዳማዊ ማርያም ሃይማኖቱ፣
ናሁ ገደፍኩ ሕይወትየ ቅድመ ተአምርኪ ዝንቱ፣
ዓለሙኒ ኃላፊ ንብረቱኒ ኃላፊ እስመ ኵሉ ኃላፊ ውእቱ።
14. ሰላም ለሥዕልኪ ዘክንፈ መላእክት ምጽላሉ፣
ወጸዳለ ክርስቶስ ስነ ጸዳሉ፣
እመ ያዕቆብ በጸጋ ማርያም እግዝእተ ኵሉ፣
ናሁ አግብርትኪ በቃለ ማኅሌት ይብሉ፣
ስብሐት ወክብር ወሰጊድ ለመንግሥትኪ ይደሉ።
15. ሰላም ለሥዕልኪ ወለሥዕለ ወልድኪ ዘሰዐሞ፣
ዮሐንስ ርኄ ዮሐንስ ቀናንሞ፣
ለዝ ወልድኪ መሐሪ ኅሩመ በቀል ወተቀይሞ፣
ማርያም ሀብኒ በእዴኪ እንዘ ትጼውዒ ስሞ፣
ሥጋሁ ቅዱሰ ወክቡረ ደሞ
16. ሰላም ለሥዕልኪ ወለሥዕለ ወልድኪ በመትሎ፣
እንተ ነገደ ወሖረ መንገለ አቃርዮስ ሀሎ፣
ኀበ ዝ ወልድኪ ፈጣሪ ናትናኤል ዘይትዌከሎ፣
ከመ የሀበኒ ጽድቆ ወይጸግወኒ ሣህሎ፣
ድንግል በእንቲአየ አብዝኂ ተንብሎ።
17.ሰላም ለሥዕልኪ ሐፈ ማኅየዌ፣
በጼዴንያ ወግብፅ ዘአውኀዘት በኢሕሣዌ
ለመጸብሐዊ ማቴዎስ ማርያም እንተ ረሰይኪዮ ወንጌላዌ፣
ይኩነኒ ወትረ ጸሎትኪ እምዘመነ ኵሉ ምንሳዌ፣
ዐቃቤ ዘመዓልት ወዘሌሊት ሀላዌ።
18. ሰላም ለሥዕልኪ ሶበ ጸለየት ማርታ፣
አጽኒና ርእሳ ከመ ትትመጦ ስእለታ፣
ምክሐ ታዴዎስ አንቲ ማርያም ወሞገሰ ቶማስ ስሙየ መንታ፣
አመ ኢታድኅን እም ወለታ ወአመ ታገብእ ምድር ማኅፀንታ፣
ኩንኒ ለመዋቲ ሐገፋ ወወልታ።
19. ሰጊድ ወአምኃ ይደሉ ለሥዕልኪ፣
ወለሥዕለ ክርስቶስ ወልድኪ፣
ወይነ በርተሎሜዎስ አንቲ ማርያም ዘያስተፌሥሕ ጣዕመ ፍቅርኪ፣
አንብርኒ ከመ ኅልቀት በውሣጤ ርኅሩኅ ልብኪ
ወከመ ማዕተብ ፁርኒ በመዝራዕትኪ።
20. ሰላም ለሥዕልኪ ዘመአድም ብርሃኑ፣
ወፍትው ሞገሰ ስኑ፣
ሃይማኖተ ፊልጶስ አንቲ ማርያም ከመ ጳውሎስ ይዜኑ፣
ሕማምኑ መጥባህትኑ ፃዕርኑ፣
አኅድጎ ፍቅርኪ ዘይክለኒ መኑ።
21. ሰላም ለሥዕልኪ ቦ ጊዜ ዘትትናገር፣
ወቦ ጊዜ ዘትክዑ ደመ ተአምር፣
ማርያም ስብሕት ወውድስት እመ እግዚአብሔር፣
ለማትያስ ሙቁሕ ወለያዕቆብ ውጉር፣
እስመ አንቲ ሞገሶሙ በሰማይ ወምድር።
22. በኢትዮጵያ ወግብፅ ወሶርያ በአንጾኪያ ወሮም፣
ለሥዕላትኪ ዘሀለዋ ማርያም ሰላም፣
ምስለ ኤጲስ ቆጶስ ያዕቆብ ዘኢየሩሳሌም፣
ይምጽኡ ኀቤነ ዘእምኀቤኪ ለባርኮትነ ዮም፣
ማርቆስ ዘአንበሳ ወሉቃስ ዘላህም።
23. ሰላም ለሥዕልኪ እንተ ሠዐላ በእዱ፣
ሉቃስ ጠቢብ ዘእምወንጌላውያን አሀዱ፣
አመ ተቀብዑ ማርያም እምሐፈ ሥዕልኪ ቅብዐ ናርዱ፣
በሕማም እኩይ እለ ደወዩ ወውህዱ፣
ፅዑራነ ዓለም ጥዕዩ ወጥቀ ፈድፈዱ።
24.  ሰላም ለሥዕልኪ ወለሥዕለ ወልድኪ አልፋ፣
ማርያም ዘኮንኪ ለኃጥአነ ምድር ተስፋ፣
እመቦ እምሰብእ ዘይሜንና ወዘይገድፋ፣
ለተአምርኪ ባቊዕ እንተ ደቅስዮስ ጸሐፋ፣
ውጉዘ ይኩን በቃሎሙ ለሳውል ወኬፋ።
25. ተማኅፀንኩ እግዝእትየ ማርያም በመልክአ ሥዕልኪ ዛቲ፣
እንዘ እሰግድ ቅድሜሃ ወእትጋነይ ላቲ፣
ማርያም ድንግል ማርያም ወለተ ማቲ፣
ቤዛ ቤዛ ቤዛ ነፍሰ ኵሉ መዋቲ፣
በሰማይኒ ወበምድር አንቲ።
26. ሰላም ሰላም ለመልክአ ሥዕልኪ ኵሉ፣
እምነ ፀሐይ ወወርኅ ዘያበርህ ስነ ፀዳሉ፣
ወበእንተዝ ማርያም ስብሐተ ዚአኪ ይብሉ፣
እስመ አባልኪ ለእግዚአብሔር አባሉ፣
ማርያም በረከትኪ ምስሌነ የሃሉ።

ያዳምጡት https://youtu.be/tobGssdKuUo

Wednesday, May 13, 2020

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ


"ተዘከሩ በዓሉ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መናኒ "
#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ
#ሃሌ_ሉያ_ነበረ_በገዳም
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
ነበረ በበረ በገዳም ወበዓታት
እንዘ ይትጌገስ ጽምዐ ወረኀበ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሕይወት.
ነበረ በገዳም ወበዓታት
እንዘ ይለብስ ጸጉረ
ከመ እንስሳ ወአራዊት
ነበረ በገዳም ወበዓታት
እንዘ ይትኤዘዙ ሎቱ ከመ አግብርት
ግሩማን አናብስት ወአናምርት
ነበረ በገዳም ወበዓታት
አኮ ዘነበረ ከመ ስብእ አላ ረሰየ
ንብረቶ ከመ መላእክት
ነበረ በገዳም ወበአታት
ቃለ ፈጣርክሁ ጸዋዒ እንበለ እረፍት
እስከ ይጼውዖ በሞት
ነበረ በገዳም ወበዓታት

ትርጉም:
በዓቱን አጽንቶ በምድረ በዳ የነበረው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ርሃብና ጥምን ታግሷል፤እንደ አራዊቶችም ጸጉርን ይለብስ ነበር፤አንበሳና ነብርም እንደ ባርያ ሆነው ይታዘዙት ነበር፤በምድር ላይ ሰው ሆኖ ሳለ በተጋድሎው እንደ መላክት ሆነ ክብርንም አገኘ፤በሞት እስከሚጠራ የመጨረሻው ህቅታ ድረስ የአምላኩን ቃል ፈጽመሟል።

Wednesday, May 6, 2020

ልደታ ለማርያም



#ቅዱስ_ክቡር_ቤተሰብ
እንዲህ ያለውን ቤተሰብ ማን ይታደለው ይሆን?
*አምላክን የምትወልድ ልጅን መውለድ ምንኛ መታደል ነው።
*ከሰው ወገን ለዚህ ክብር የተመረጠ ብቸኛ ቤተሰብ የቅዱስ ኢያቄምና የቅድስት ሐና ብቻ ነው።
*ሰው ልጁን አስተምሮ ለወግ ለማረግ ሲበቃለት ደስ ይለዋል፤ልጃቸው ያለ ወንድ ዘር በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሰማይን አምላክ የወለደችላቸው ቅዱስ ኢያቄም እና ቅድስት ቅድስት ሐና ምንኛ ይደሰቱ ይሆን?
*ሰው ልጁ አድጎ ሲሾምለት፣ ሲሸለምለት እናም ከፍ ከፍ ሲልለት ደስ ይለዋል፤አምላካችን እግዚአብሔር  ድንግል ማርያምን ሲመርጣት እናቱ ሲያደርጋት ቅዱስ ኢያቄም እና ቅድስት ሐና ምንኛ ተደስተው ይሆን?
*ሰው ልጁ በመንፈሳዊ ህይወቱ ከፍ ያለ ደረጃ ሲደርስለት በማዕረገ ክህነት ሲሾም ሲከብር ከፍ ሲል  ይደሰታል፤አንቺ ከኪሩቤልና ከሱራፌል ትበልጫለሽ፤መጽሐፍትም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለሽ አንቺ ነሽ፤ መባልን ያገኘችላቸው  ልጃቸው ቅድስት ድንግል ማርያም መሆንዋን ሲሰሙ ቅዱስ ኢያቄም እና ቅድስት ሐና ደስታውን እንዴት ችለውት ይሆን።
*የልጅ ልጃቸውን አድጎ ሲያዩ #አያቶች ይደሰታሉ፤ሰማይን ለፈጠረ አምላክ ፣ የሰው ወገንን ሁሉ ለፈጠረ አምላክ አያቱ የሆኑ ቅዱስ ኢያቄምና። ቅድስት ሐና እረ እንደው እንዴት ይሆን ደስታቸው።
ኤፍሬም ዘልደታ በእኔ ሚያዝያ 28|2012 ዓ.ም ለእናታችን ዝክረ ልደት ይሁን።

©ስነ ስዕሉ የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ራሽያ።

Tuesday, May 5, 2020

ኪርያላይሶን ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ

ልደታ ደብረ መድኅኒት መድኃኔዓለም አዲስ አበባ።

ኪርያላይሶን/8/
°°°°
እስቲ ላስታውሰው ጌታዬን
በማዘን በማልቀስ
ለሰው ሲል የሞተ
የማይሞተው ንጉሥ
ሲከሰስ በአውደ ጲላጦስ ስብሐት ለከ
°°°°
ያ አንደበትህ ጣፋጭ
ለምጽና አንካሳ የሚፈውስ
በጲላጦስ ተጠየቀ እንዲሰጥ የቃል መልስ
የእኛ ሥራ አበቃህ ለክስ ወዮ ወዮ
°°°°
እነዚያ ቅዱሳን እጆችህ
ዓለሙን ሁሉ የሰሩ
ተዓምራት በማድረግ እውራን ያበሩ
በመስቀል ላይ ተቸነከሩ ስብሐት ለከ
°°°°
ኃጢአትን ለመደምሰስ እግሮችህ በዮርዳኖስ የገቡ
እንደ ወንጀለኛ ሆኑ በጲላጦስ ፊት
በእኛ ጥፋት ስለኛ ኃጢአት አቤት አቤት
°°°°
ከላይ ከሰማያት ወርደህ
የሰው ልጅ ፍቅር አስገድዶህ
ፍዳና መከራ ስቃይን ተቀበለክ
በዘጠኝ ሰዓት ነፍስህ ሰጠህ አንተም ተፈጸመ አልክ
     
   
 ምንጩ የዚሁ ብሎግ አዘጋጅ እዚህ በመጫን ድምጹን ይስሙ : http://t.me/orthodoxzema
      

ክፍላተ አካል

ክፍል ሁለት

ክፍላተ አካል 

በፊት ያሉ የአካል ክፍሎች!!!

፩ መልክዕ       -  መልክ
፪ እልቅት        - እልቅት
፫ እንግድዓ     - ደረት
፬ ጥብ           -ጡት 
፭  ሕፅን         -ብብት
፮ ሕንብርት     -ጉብር
፯  ሐገዝ         - ጉያ 
፰  ሙሐይት   - ሙሃሂት
፱  ኀምስ       -  ሴቴ ብልት
፲  ፈርግ        -ፍርንትት
፲፩  እስኪት     -ወንዴ ብልት 
፲፪ ቁይጽ        - ጭን
፲፫  ብርክ        -ጉልበት 
፲፬  አንጉዕ       -ቅልጥም
፲፭  አፅባዕተ እግር   -የእግር ጣት
፲፮  ክሣድ            -አንገት
፲፯  አፅባዕተ እድ  - የእጅ ጣት
ይቀጥላል.......

ምንጭ :ጉባዔ አርድእት

Monday, May 4, 2020

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


"ወዳጄ ሆይ! እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ መስጠትን እንድትለማመድ ነው፡፡ ዛሬ በነዳያኑ አድሮ የሚለምንህ ለኋለኛይቱ ቀን ስንቅ እንዲያስቀምጥልህ ወድዶ ነው፡፡ ታድያ ንጉሥ ወደ ቤቱ መጥቶ የሚያባርር ሰው እንደምን ያለ ጎስቋላ ሰው ነው? እንግዲያውስ ነዳያንን ስታይ ወደ አንተ የመጣው ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ እንጂ ሰው አይደለምና አትግፋው፡፡ በረከትህንም ከቤትህ አውጥተህ አትሸኘው፡፡"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"አንድ ነዳይ አጥብቆ እየለመነህ በቸልታ ትተኸው ስትሔድ እግዚአብሔርን አጥብቀህ በምትለምን ጊዜ ቢተውህ የሚሰማህን አስብ።"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"እንደ ሰውነታችን ዕለት ዕለት እንበድላለን፡፡ በጥምቀት ያገኘነውን ልጅነት እናቆሽሸዋለን፡፡ አዲሱን ሰውነታችን ብሉይ እናደርገዋለን፡፡ ነገር ግን ይህን ዕለት ዕለት ማደስ ይቻላል፡፡ አንድ ቤት እያረጀ ቢሄድ እንደ አዲስ እንሠራዋለን፡፡ ክዳኑን፣ ቀለሙን፣ ምንጣፉን እድሳት እናደርግለታለን፡፡ እኛም በኃጢአት ባረጀው ሰውነታችን ላይ እንዲህ ልናደርግ ይገባናል በንስሐ፡፡"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል፡፡"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ



የቅዱስ ያሬድ የዜማ ምልክቶች

የቅዱስ ያሬድ የዜማ ምልክቶችና ሚስጥራቸው!
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያናችን ካፈራቻቸውና ለአገርና ለቤተክርስቲያን ዘመን ተሻጋሪ ጉልህ አስተዋጽኦ ካበረከቱት ሊቃውንት መካከል አንደኛውና በቀዳሚነት የሚጠቀስ አባት ነው። ቅዱስ ያሬድ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበትን የዜማ ስልት ያረቀቀ ሊቅ ሲሆን እነዚህ የዜማ ሥልቶችም ከሰማይ የተቀበላቸው ሲሆኑ ግእዝ፣ ዕዝልና አራራይ በመባል ይታወቃሉ። ቅዱስ ያሬድ እነሞዛርትና ቤትሆቭን ከመነሣታቸው ከሺህ ዓመታት አስቀድሞ ተፈጥሯዊ ዜማን በምልክት የገለጸና የዜማ ሥልቶችን በሥርዓት ያረቀቀ ዕውቅ የዜማ ሊቅ ነው።
ከዜማ ስልቶቹ በተጨማሪ ቅዱስ ያሬድ የተለያዩ መጽሐፍትን በመድረስ ለቤተክርስቲያን አበርክቷል። ከደረሳቸው መጽሐፍት መካከልም ድጓ፣ ፆመ ድጓ፣ ዝማሬ መዋሥዕት ወዘተ ይገኙበታል። ሉቁ በድጓ መጽሐፉ ላይ የዐቢይ ፆም ሳምንታትን የየራሳቸው ስያሜ ሰጥቷቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ጸዋትወ መከራ ለማሰብ ስምንቱን የዜማምልክቶች በመጽሐፎቹ ላይ አስቀምጧልናል። እነዚህ የዜማ ምልክቶች በቁጥር ስምንት የሆኑበተሰ ዐቢይ ምክንያት ስምንቱ ማኅበረ አይሁድ ተባብረውና መክረው በብዙ ስቃይ ጌታችንን መስቀላቸውና መግደላቸውን ለማሰብ ነው። እነዚህ ማኅበረ አይሁድ የሚባሉትም
፩] ጸሐፍት ፈሪሳዊያን
፪] ሰዱቃውያን
፫] ረበናት (መምህራነ አይሁድ)
፬] መገብተ ምኩራብ (የምኩራብ ሹማምንት)
፭] መላሕቅተ ሕዝብ (የሕዝብ ሽማግሌዎች)
፮] ሊቃነ ካህናት
፯] ኃጥአን እና
፰] መጻብሓን (ቀራጮች) ናቸው።
ቅዱስ ያሬድ ለቤተክርስቲያናችን ያበረከታቸው ስምንቱ የዜማ ምልክቶችም
፩} ይዘት - በአይሁድ ጭፍሮች ለመያዙ (ማቴ 26:50)
፪} ሂደት - ታሥሮ ለመጐተቱ
፫} ጭረት - ለግርፋቱ ሰምበር
፬} ድፋት - የእሾህ አክሊል ለመድፋቱ
፭} ደረት - መስቀል ላይ አንጋለው ደረቱ ላይ ረግጠው ስለመቸንከራቸው
፮} ርክርክ - ስለደሙ ነጠብጣብና አወራረድ
፯} ቁርጥ - በጦር ተወግቶ ፈጽሞ መሞቱ ስለመታወቁ ወይም አይሁዳውያን ጌታችንን ለመስቀል ቁረሰጥ ውሳኔ ስለመወሰናቸው
፰} ቅንዓት - በቅንዓተ አይሁድ ለመገደሉ ምልክቶችና ማስታወሻ ምሳሌዎች ናቸው!
ይሁን እንጂ ቅዱስ ያሬድ ከእነሞዛርትና ቤትሆቨን የቀደመ ሊቅ ሆኖ ሳለ ዛሬም ድረስ ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና እንዲኖር ስላልተሠራ በቤተክርስቲያን ሊቃውንት ዘንድ ብቻ ተወስኖ እንዲቀር ሆኗል። የቅዱስ ያሬድን ሥራዎች ለዓለም በመመስከርና ሊቁን በማስተዋወቅ የኢትዮጵያን ልዕልና ዓለም እንዲያውቀው ለማድረግ እያንዳንዳችን የበኩላችንን መወጣት ይኖርብናል። ይህን ማድረግ የምንችለው ደግሞ አስቀድመን እኛ ሊቁንና ሥራዎቹን ማወቅ ስንችል ነውና ሊቁን እንወቀው። የልዑል እግዚአብሔር ቸርነትና የቅዱስ ያሬድ በረከት ከኹላችን ጋር ይሁን አሜን።
© ዳንኤል ገብረማርያም