ዜማ ቤት
ቅኔ ማህሌት፡- የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ሊቃውንትና ካህናት ለአምላክ ምስጋና ማህሌት የሚያደርሱበት ስፍራነወ፡፡
ንባብ ቤት፡-ፊደል ቆጠራ፣የቁጥር ትምህርት፣ፊደሎችን አገጣጥሞ
ማንበብ፣መሰረተ ሀይማኖት
ሲሆኑ፣ትምህርቱን ለመጠናቀቅ
ከ2-3 ዓመት ይፈጃል፡፡
ዜማቤት፡- የትምህርት ይዘቱ ቅዳሴን ጨምሮ ልዩልዩ የዜማ አይነቶችን ያካትታል፣ዋና ዋናወቹ ፣ጾመድጓ፣ምዕራፍ፣ዝማሬና መዋስዕት
፣አቋቋም ፣ቅዳሴ ናቸው፡፡አንዳንዳቸው
በልዩ ልዩ ሊቃውንትና መምህራን ይጠናሉ፡፡
ቅኔ ቤት፡- የትምህርት ይዘቶች በግስ እርባታ እና ሰዋ ሰው አካሄዶች በቅኔ አገባብ ፣በቅኔ አይነትና አመስጥሮ ላይ የሚያተኩር ሲሆን እያንዳንዳቸውም በልዩ ልዩ መምህራን ስር ይጥናሉ፡፡
መጽሀፍ
ቤት፡- መጻህፍተ ብሉያት፣መጻህፍት ሀዲስ፣መፃፍተ
ሊቃውንት ፣መፃህፍተ
መነኮሳት የተባለ የጥናት መስኮችን ያካትታል፡፡እነዚህን አራቱን ጠንቅቀው የሚመረቁ ጥቂት ብርቱዎችና ትጉሀን ሲሆኑ ‹‹የአራት ጉባኤ መምህር ››ወይም አራት አይና ተብለው ይጠራሉ፡፡
ይቆየን....
No comments:
Post a Comment