Wednesday, May 6, 2020

ልደታ ለማርያም



#ቅዱስ_ክቡር_ቤተሰብ
እንዲህ ያለውን ቤተሰብ ማን ይታደለው ይሆን?
*አምላክን የምትወልድ ልጅን መውለድ ምንኛ መታደል ነው።
*ከሰው ወገን ለዚህ ክብር የተመረጠ ብቸኛ ቤተሰብ የቅዱስ ኢያቄምና የቅድስት ሐና ብቻ ነው።
*ሰው ልጁን አስተምሮ ለወግ ለማረግ ሲበቃለት ደስ ይለዋል፤ልጃቸው ያለ ወንድ ዘር በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሰማይን አምላክ የወለደችላቸው ቅዱስ ኢያቄም እና ቅድስት ቅድስት ሐና ምንኛ ይደሰቱ ይሆን?
*ሰው ልጁ አድጎ ሲሾምለት፣ ሲሸለምለት እናም ከፍ ከፍ ሲልለት ደስ ይለዋል፤አምላካችን እግዚአብሔር  ድንግል ማርያምን ሲመርጣት እናቱ ሲያደርጋት ቅዱስ ኢያቄም እና ቅድስት ሐና ምንኛ ተደስተው ይሆን?
*ሰው ልጁ በመንፈሳዊ ህይወቱ ከፍ ያለ ደረጃ ሲደርስለት በማዕረገ ክህነት ሲሾም ሲከብር ከፍ ሲል  ይደሰታል፤አንቺ ከኪሩቤልና ከሱራፌል ትበልጫለሽ፤መጽሐፍትም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለሽ አንቺ ነሽ፤ መባልን ያገኘችላቸው  ልጃቸው ቅድስት ድንግል ማርያም መሆንዋን ሲሰሙ ቅዱስ ኢያቄም እና ቅድስት ሐና ደስታውን እንዴት ችለውት ይሆን።
*የልጅ ልጃቸውን አድጎ ሲያዩ #አያቶች ይደሰታሉ፤ሰማይን ለፈጠረ አምላክ ፣ የሰው ወገንን ሁሉ ለፈጠረ አምላክ አያቱ የሆኑ ቅዱስ ኢያቄምና። ቅድስት ሐና እረ እንደው እንዴት ይሆን ደስታቸው።
ኤፍሬም ዘልደታ በእኔ ሚያዝያ 28|2012 ዓ.ም ለእናታችን ዝክረ ልደት ይሁን።

©ስነ ስዕሉ የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ራሽያ።