ልሳነ አበው
√ ‹‹ እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ ›› አባ እንጦንስ
√ ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻለን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻለናል›› ቅዱስ አትናቴዎስ
√ ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስን ጸጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢአተኞች የሚገቡበት የገሃነም እሳት ግን ለዘላለም እንዲሁ ይኖራል፡፡›› ቅዱስ ሚናስ
√ ‹‹በማንም ላይ ክፋትን አትሥሩ አትፍረዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና›› ታላቁ አባ መቃርስ
√ ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናለሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም›› ቅዱስ አርሳንዮስ
√ ‹‹ቤተክርስቲያን መጠሪያችን ነች ፤ ቤተ ክርስቲያን
የኖኅ መርከብ ነች ፤ በውስጧ እንጠለላለን ከውጪው ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል›› ቅዱስ እንድርያስ
√ ‹‹ሥጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ሕይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው›› ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዮስ ካልዕ
√ ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከሆነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ንጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስ ቅዱስ የተሞላን እንሆናለን ›› አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን
√ ‹‹የቤተክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተ ክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ›› ብፁዑ አቡነ ጎርጎሪዮ ካልዕ
√ ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ጸሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊትን በሙሉ ስትጸልይ እደር›› ቅዱስ ይስሐቅ ሶሪያዊ
√ ‹‹ኃጢአታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጢአታችንን እኛ እረስተን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል›› ቅዱስ እንጦንስ
√ ‹‹ራስህን በሐሰት አትውቀስ፤ ራስን መክሰስ ትህትና አይደልም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ ነው›› ቅዱስ ስራፕዋን
√ ‹‹አንደበቱን ከቧልት ፣ ከሐሜት ፣
ያየውንም ምሥጢር ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከሃልዮ ኃጢአት ያርቀዋል፡፡›› አርጋዊ መንፈሳዊ
√ ‹‹የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትሥራው ከሠራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ›› መጽሐፈ ምክር
√ ‹‹ጸጋ ሲሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ›› ማር ይስሐቅ
√ ‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል ፤ አዋቂ ነኝ
የሚል ሰው ከፈጣሪው ጥበብ ይለገሳል፡፡›› አረጋዊ መንፈሳዊ
ይቆየን....
No comments:
Post a Comment