ቅኔ:
ኢትእመኑ ህዝብ ዘወለድክሙ በተድላ
እስመ ለማርያም ድንግል ዘወለደቶ ቀተላ
ትርጉም:
ወገኖቼ (ህዝቦች ሆይ) በደስታ የወለዳችሁትን አትመኑት
ለድንግል ማርያምም የወለደችው ገድሏታልና
ትንታኔ:
አንዳንድ እናቱን የሚገድል ልጅ እንደማይታጣ ሁሉ በሰው ፊት ለማንም የማያዳላ አምላክ በአዳምና በሄዋን የፈረደውን የስጋ ሞት እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም እንድትቀምሰው አደረገ ።ይላሉ ባለቅኔው።
No comments:
Post a Comment