Pages

Pages

Saturday, April 25, 2020

ዶግማ

ቃሉ የግሪክ ሲሆን ፍችውም እምነት ማለት ነው፡፡ ቀኖና፡- ደግሞ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ሥርዓት ማለት ነው፡፡ትውፊት ፦ አወፈየ ከሚለው የግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ውርስ ቅብብል ማለት ነው። ዶግማ ወይም እምነት አይጨመርበትም፤ አይቀነስበትም፤ አይሻሻልም፤ ችግርና ፈተናም ቢመጣ እስከ ሞት ድረስ አጥብቀን የምንይዘው ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፦ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረ፤ ቢመረምር እንጂ የማይመረመር ሁሉን ቻይ አምላክ፤ የሚሳነው ነገር የሌለ ፈጣሪ፤ የሰማይና የምድር ባለቤት የሠራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔር ነው፡፡እግዚአብሔር (ፈጣሪ) የአካል ሦስትነት አለው፡፡ በመለኮት፣ በመፍጠር፣ በሥልጣን፣ በአገዛዝ፣ በፈቃድ ግን አንድ ነው፡፡ በሦስትነቱ አብ፤ ወልድ፤ መንፈስ ቅዱስ ሲባል በአንድነቱ አንድ መለኮት አንድ እግዚአብሔር ይባላል፡፡በአዳም ምክንያት ከመጣው የዘለዓለም ሞትና ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ የወጣነው ከሦስቱ አካላት በአንደኛው አካል ማለትም በወልድ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህ ዶግማ ወይም እምነት ይባላል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር::

ቅዱስ እስጢፋኖስ

ዛሬ እኮ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነው:: ሰአለ ስረይ ለኃጢአት ለእለ ወገርዎ ወይቤ ስረይ ሎሙ ዘንተ ኃጢአቶሙትርጉም:ለሚወግሩት ሰዎች ኃጢያታቸውን ይቅር በል ብሎ ለመነላቸው።“ተንበርክኮም፦ ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ፦ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር።”ሐዋርያት 7፥60 ቅዱስ ሰማዕት ቀዳሜ ሰማዕት ሊቀ ዲያቆን እስጢፋኖስ በረከቱ ይደርብን።