Pages

Pages

Saturday, May 16, 2020

መልክአ ሥዕል


1. ምንተኑ አዓሥየኪ ዕሤተ፣
በእንተ ኵሉ ዘገበርኪ ሊተ፣
ማርያም ሠናይት ዘታፈቅሪ ምሕረተ፣
ሶበሰ ተትዓቀቢ ዘዚአየ ኃጢአተ፣
እምኢሐዮኩ አሐተ ሰዓተ።
2. በሰላመ ገብርኤል መልአክ ኦ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ፣
ድንግል በኅሊናኪ ወድንግል በሥጋኪ፣
እመ እግዚአብሔር ጸባዖት ሰላም ለኪ፣
ቡርክት አንቲ እምአንስት ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ፣
ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ።
3. ኦ ርኅሩኀነ ልቡና አፍቅሮተ ሰብእ ልማድክሙ፣
በጥቡዕ ልብ ንስእለክሙ፣
ሥሉስ ቅዱስ ምሕረተክሙ አዝንሙ፣
ክሣደ ፀርነ በሰይፍክሙ ግዝሙ፣
ወዲበ ርእስነ ዓዲ እዴክሙ ሢሙ።
4. ኦ ርኅርኅተ ኅሊና አፍቅሮተ ሰብእ ልማዳ፣
ሰአሊተ ምሕረት ይእቲ ማርያም ሐፁረ መስቀል ዘየዓውዳ፣
ንትቀበላ ንዑ ለወለተ ዳዊት ዘይሁዳ፣
መጽአት ነዋ ኅቡረ ምስለ ወልዳ፣
ናንፈርዕፅ ቅድመ ሥዕላ እንዘ ንሁብ ጋዳ፣
ለለጌሠሙ ትመስል እንግዳ።
5. ኦ ርኅርኅተ ኅሊና ዘሕገ ልማዳ ምሕረት፣
ለኵሉ ፍጥረት፣
ንሳለማ ንዑ ለሥዕለ ማርያም ቡርክት፣
ወለሥዕለ ወልዳ ጸባዖት ወለሥዕለ ጊዮርጊስ ሰማዕት፣
ሥዕለ ሚካኤል ወገብርኤል ወሩፋኤል ዘራማ ኃይላት።
6. ኦ ርኅርኅተ ኅሊና ፍቅርኪ ያነድድ አማዑተ፣
ከዊኖ እሳተ፣
ንጽሐ ድንግልናኪሰ እንተ ኢያእመረ ርስሐተ፣
ማርያም ግበሪ ሠናያተ ኵሎ ዕለተ፣
ሞትሰ ድልው ሊተ፣
ባሕቱ ለንሥሓ ጽንሕኒ ንስቲተ።
7. ኦ ርኅርኅተ ኅሊና ለእግዚአብሔር አስከሬኑ፣
እንተ ኢያውዓየኪ እሳተ ርስኑ፣
መሐርኒ ድንግል ወተሣሃልኒ በበዘመኑ፣
ለእመ መሐርክኒ እግዝእትየ ዘይኴንነኒ መኑ፣
ኰናኔ ሥጋ ወነፍስ ወልድኪ አኮኑ።
8. ኦ ርኅርኅተ ኅሊና እንተ ኤልያስ ደመና፣
ወለተ ኢያቄም ወሐና፣
ማርያም ዑጽፍት ወኁብርት በቅድስና፣
ሶበ ነጸረኪ ሙሴ በሲና፣
ኅትምት በድንግልና አልባቲ ሙስና።
9. ተአምርኪ ብዙኅ ዘአልቦ ፍጻሜ፣
በርኅበ ዓለም ሰፈነ አምሳለ ደመና ወጊሜ፣
ማርያም ድንግል ደብተራ ጳውሎስ ዘብሔረ ሮሜ፣
ተማሕፀንኩ በሕፃንኪ ዘሐዘለቶ ሰሎሜ፣
እንበለ ንሥሓ ኢይሙት ወስክኒ እድሜ።
10. ቅድመ ሥዕልኪ እሰግድ ወአስተበርክ ክሡተ፣
ቅድመ ማኅበራንኪ እሉ እንዘ እቀውም ድርገተ፣
ፈጻሚተ መፍቅድ ማርያም እስእለኪ ስእለተ፣
ጸግውኒ እግዝእትየ ለዓለመ ዓለም ሕይወተ፣
እምእደ እኩያን አፅራርየ አድኅንኒ ሊተ።
11.ቅድመ ሥዕልኪ እሰግድ ወለሥዕለ ወልድኪ እገኒ፣
ማርያም ድንግል ማርያም እመ አዶኒ፣
ማዕበለ ጌጋይ ጽኑዕ ሶበ ለአስጥሞ በጽሐኒ፣
ሐመርየኒ ማዕዶትየኒ ሃይማኖትየኒ፣
ማርያም ዘእንበሌኪ አልብየ ምንትኒ።
12. ሰላም ለሥዕልኪ ዘይኤድም ለንጻሬ፣
ዓዲ ሰላም ወለሥዕለ ወልድኪ በኁባሬ፣
አክሊለ ሢመቱ ለጴጥሮስ ማርያም እንተ ትፀድሊ እምወራውሬ፣
ለተአምርኪ ባቊዕ ሶበ ናቄርብ ዝማሬ ፣
ክድንነ ለአግብርትኪ ሣህለኪ ጶደሬ።
13. ሰላም ለሥዕልኪ መዓዛ ቅዳሴ ዘቦቱ፣
ወለሥዕለ ወልድኪ ሰላም ዘያስተፌሥሕ ስነ ርእየቱ፣
ለሐዋርያ እንድርያስ ቀዳማዊ ማርያም ሃይማኖቱ፣
ናሁ ገደፍኩ ሕይወትየ ቅድመ ተአምርኪ ዝንቱ፣
ዓለሙኒ ኃላፊ ንብረቱኒ ኃላፊ እስመ ኵሉ ኃላፊ ውእቱ።
14. ሰላም ለሥዕልኪ ዘክንፈ መላእክት ምጽላሉ፣
ወጸዳለ ክርስቶስ ስነ ጸዳሉ፣
እመ ያዕቆብ በጸጋ ማርያም እግዝእተ ኵሉ፣
ናሁ አግብርትኪ በቃለ ማኅሌት ይብሉ፣
ስብሐት ወክብር ወሰጊድ ለመንግሥትኪ ይደሉ።
15. ሰላም ለሥዕልኪ ወለሥዕለ ወልድኪ ዘሰዐሞ፣
ዮሐንስ ርኄ ዮሐንስ ቀናንሞ፣
ለዝ ወልድኪ መሐሪ ኅሩመ በቀል ወተቀይሞ፣
ማርያም ሀብኒ በእዴኪ እንዘ ትጼውዒ ስሞ፣
ሥጋሁ ቅዱሰ ወክቡረ ደሞ
16. ሰላም ለሥዕልኪ ወለሥዕለ ወልድኪ በመትሎ፣
እንተ ነገደ ወሖረ መንገለ አቃርዮስ ሀሎ፣
ኀበ ዝ ወልድኪ ፈጣሪ ናትናኤል ዘይትዌከሎ፣
ከመ የሀበኒ ጽድቆ ወይጸግወኒ ሣህሎ፣
ድንግል በእንቲአየ አብዝኂ ተንብሎ።
17.ሰላም ለሥዕልኪ ሐፈ ማኅየዌ፣
በጼዴንያ ወግብፅ ዘአውኀዘት በኢሕሣዌ
ለመጸብሐዊ ማቴዎስ ማርያም እንተ ረሰይኪዮ ወንጌላዌ፣
ይኩነኒ ወትረ ጸሎትኪ እምዘመነ ኵሉ ምንሳዌ፣
ዐቃቤ ዘመዓልት ወዘሌሊት ሀላዌ።
18. ሰላም ለሥዕልኪ ሶበ ጸለየት ማርታ፣
አጽኒና ርእሳ ከመ ትትመጦ ስእለታ፣
ምክሐ ታዴዎስ አንቲ ማርያም ወሞገሰ ቶማስ ስሙየ መንታ፣
አመ ኢታድኅን እም ወለታ ወአመ ታገብእ ምድር ማኅፀንታ፣
ኩንኒ ለመዋቲ ሐገፋ ወወልታ።
19. ሰጊድ ወአምኃ ይደሉ ለሥዕልኪ፣
ወለሥዕለ ክርስቶስ ወልድኪ፣
ወይነ በርተሎሜዎስ አንቲ ማርያም ዘያስተፌሥሕ ጣዕመ ፍቅርኪ፣
አንብርኒ ከመ ኅልቀት በውሣጤ ርኅሩኅ ልብኪ
ወከመ ማዕተብ ፁርኒ በመዝራዕትኪ።
20. ሰላም ለሥዕልኪ ዘመአድም ብርሃኑ፣
ወፍትው ሞገሰ ስኑ፣
ሃይማኖተ ፊልጶስ አንቲ ማርያም ከመ ጳውሎስ ይዜኑ፣
ሕማምኑ መጥባህትኑ ፃዕርኑ፣
አኅድጎ ፍቅርኪ ዘይክለኒ መኑ።
21. ሰላም ለሥዕልኪ ቦ ጊዜ ዘትትናገር፣
ወቦ ጊዜ ዘትክዑ ደመ ተአምር፣
ማርያም ስብሕት ወውድስት እመ እግዚአብሔር፣
ለማትያስ ሙቁሕ ወለያዕቆብ ውጉር፣
እስመ አንቲ ሞገሶሙ በሰማይ ወምድር።
22. በኢትዮጵያ ወግብፅ ወሶርያ በአንጾኪያ ወሮም፣
ለሥዕላትኪ ዘሀለዋ ማርያም ሰላም፣
ምስለ ኤጲስ ቆጶስ ያዕቆብ ዘኢየሩሳሌም፣
ይምጽኡ ኀቤነ ዘእምኀቤኪ ለባርኮትነ ዮም፣
ማርቆስ ዘአንበሳ ወሉቃስ ዘላህም።
23. ሰላም ለሥዕልኪ እንተ ሠዐላ በእዱ፣
ሉቃስ ጠቢብ ዘእምወንጌላውያን አሀዱ፣
አመ ተቀብዑ ማርያም እምሐፈ ሥዕልኪ ቅብዐ ናርዱ፣
በሕማም እኩይ እለ ደወዩ ወውህዱ፣
ፅዑራነ ዓለም ጥዕዩ ወጥቀ ፈድፈዱ።
24.  ሰላም ለሥዕልኪ ወለሥዕለ ወልድኪ አልፋ፣
ማርያም ዘኮንኪ ለኃጥአነ ምድር ተስፋ፣
እመቦ እምሰብእ ዘይሜንና ወዘይገድፋ፣
ለተአምርኪ ባቊዕ እንተ ደቅስዮስ ጸሐፋ፣
ውጉዘ ይኩን በቃሎሙ ለሳውል ወኬፋ።
25. ተማኅፀንኩ እግዝእትየ ማርያም በመልክአ ሥዕልኪ ዛቲ፣
እንዘ እሰግድ ቅድሜሃ ወእትጋነይ ላቲ፣
ማርያም ድንግል ማርያም ወለተ ማቲ፣
ቤዛ ቤዛ ቤዛ ነፍሰ ኵሉ መዋቲ፣
በሰማይኒ ወበምድር አንቲ።
26. ሰላም ሰላም ለመልክአ ሥዕልኪ ኵሉ፣
እምነ ፀሐይ ወወርኅ ዘያበርህ ስነ ፀዳሉ፣
ወበእንተዝ ማርያም ስብሐተ ዚአኪ ይብሉ፣
እስመ አባልኪ ለእግዚአብሔር አባሉ፣
ማርያም በረከትኪ ምስሌነ የሃሉ።

ያዳምጡት https://youtu.be/tobGssdKuUo

Wednesday, May 13, 2020

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ


"ተዘከሩ በዓሉ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መናኒ "
#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ
#ሃሌ_ሉያ_ነበረ_በገዳም
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ
ነበረ በበረ በገዳም ወበዓታት
እንዘ ይትጌገስ ጽምዐ ወረኀበ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሕይወት.
ነበረ በገዳም ወበዓታት
እንዘ ይለብስ ጸጉረ
ከመ እንስሳ ወአራዊት
ነበረ በገዳም ወበዓታት
እንዘ ይትኤዘዙ ሎቱ ከመ አግብርት
ግሩማን አናብስት ወአናምርት
ነበረ በገዳም ወበዓታት
አኮ ዘነበረ ከመ ስብእ አላ ረሰየ
ንብረቶ ከመ መላእክት
ነበረ በገዳም ወበአታት
ቃለ ፈጣርክሁ ጸዋዒ እንበለ እረፍት
እስከ ይጼውዖ በሞት
ነበረ በገዳም ወበዓታት

ትርጉም:
በዓቱን አጽንቶ በምድረ በዳ የነበረው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ርሃብና ጥምን ታግሷል፤እንደ አራዊቶችም ጸጉርን ይለብስ ነበር፤አንበሳና ነብርም እንደ ባርያ ሆነው ይታዘዙት ነበር፤በምድር ላይ ሰው ሆኖ ሳለ በተጋድሎው እንደ መላክት ሆነ ክብርንም አገኘ፤በሞት እስከሚጠራ የመጨረሻው ህቅታ ድረስ የአምላኩን ቃል ፈጽመሟል።

Wednesday, May 6, 2020

ልደታ ለማርያም



#ቅዱስ_ክቡር_ቤተሰብ
እንዲህ ያለውን ቤተሰብ ማን ይታደለው ይሆን?
*አምላክን የምትወልድ ልጅን መውለድ ምንኛ መታደል ነው።
*ከሰው ወገን ለዚህ ክብር የተመረጠ ብቸኛ ቤተሰብ የቅዱስ ኢያቄምና የቅድስት ሐና ብቻ ነው።
*ሰው ልጁን አስተምሮ ለወግ ለማረግ ሲበቃለት ደስ ይለዋል፤ልጃቸው ያለ ወንድ ዘር በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሰማይን አምላክ የወለደችላቸው ቅዱስ ኢያቄም እና ቅድስት ቅድስት ሐና ምንኛ ይደሰቱ ይሆን?
*ሰው ልጁ አድጎ ሲሾምለት፣ ሲሸለምለት እናም ከፍ ከፍ ሲልለት ደስ ይለዋል፤አምላካችን እግዚአብሔር  ድንግል ማርያምን ሲመርጣት እናቱ ሲያደርጋት ቅዱስ ኢያቄም እና ቅድስት ሐና ምንኛ ተደስተው ይሆን?
*ሰው ልጁ በመንፈሳዊ ህይወቱ ከፍ ያለ ደረጃ ሲደርስለት በማዕረገ ክህነት ሲሾም ሲከብር ከፍ ሲል  ይደሰታል፤አንቺ ከኪሩቤልና ከሱራፌል ትበልጫለሽ፤መጽሐፍትም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለሽ አንቺ ነሽ፤ መባልን ያገኘችላቸው  ልጃቸው ቅድስት ድንግል ማርያም መሆንዋን ሲሰሙ ቅዱስ ኢያቄም እና ቅድስት ሐና ደስታውን እንዴት ችለውት ይሆን።
*የልጅ ልጃቸውን አድጎ ሲያዩ #አያቶች ይደሰታሉ፤ሰማይን ለፈጠረ አምላክ ፣ የሰው ወገንን ሁሉ ለፈጠረ አምላክ አያቱ የሆኑ ቅዱስ ኢያቄምና። ቅድስት ሐና እረ እንደው እንዴት ይሆን ደስታቸው።
ኤፍሬም ዘልደታ በእኔ ሚያዝያ 28|2012 ዓ.ም ለእናታችን ዝክረ ልደት ይሁን።

©ስነ ስዕሉ የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ራሽያ።

Tuesday, May 5, 2020

ኪርያላይሶን ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ

ልደታ ደብረ መድኅኒት መድኃኔዓለም አዲስ አበባ።

ኪርያላይሶን/8/
°°°°
እስቲ ላስታውሰው ጌታዬን
በማዘን በማልቀስ
ለሰው ሲል የሞተ
የማይሞተው ንጉሥ
ሲከሰስ በአውደ ጲላጦስ ስብሐት ለከ
°°°°
ያ አንደበትህ ጣፋጭ
ለምጽና አንካሳ የሚፈውስ
በጲላጦስ ተጠየቀ እንዲሰጥ የቃል መልስ
የእኛ ሥራ አበቃህ ለክስ ወዮ ወዮ
°°°°
እነዚያ ቅዱሳን እጆችህ
ዓለሙን ሁሉ የሰሩ
ተዓምራት በማድረግ እውራን ያበሩ
በመስቀል ላይ ተቸነከሩ ስብሐት ለከ
°°°°
ኃጢአትን ለመደምሰስ እግሮችህ በዮርዳኖስ የገቡ
እንደ ወንጀለኛ ሆኑ በጲላጦስ ፊት
በእኛ ጥፋት ስለኛ ኃጢአት አቤት አቤት
°°°°
ከላይ ከሰማያት ወርደህ
የሰው ልጅ ፍቅር አስገድዶህ
ፍዳና መከራ ስቃይን ተቀበለክ
በዘጠኝ ሰዓት ነፍስህ ሰጠህ አንተም ተፈጸመ አልክ
     
   
 ምንጩ የዚሁ ብሎግ አዘጋጅ እዚህ በመጫን ድምጹን ይስሙ : http://t.me/orthodoxzema
      

ክፍላተ አካል

ክፍል ሁለት

ክፍላተ አካል 

በፊት ያሉ የአካል ክፍሎች!!!

፩ መልክዕ       -  መልክ
፪ እልቅት        - እልቅት
፫ እንግድዓ     - ደረት
፬ ጥብ           -ጡት 
፭  ሕፅን         -ብብት
፮ ሕንብርት     -ጉብር
፯  ሐገዝ         - ጉያ 
፰  ሙሐይት   - ሙሃሂት
፱  ኀምስ       -  ሴቴ ብልት
፲  ፈርግ        -ፍርንትት
፲፩  እስኪት     -ወንዴ ብልት 
፲፪ ቁይጽ        - ጭን
፲፫  ብርክ        -ጉልበት 
፲፬  አንጉዕ       -ቅልጥም
፲፭  አፅባዕተ እግር   -የእግር ጣት
፲፮  ክሣድ            -አንገት
፲፯  አፅባዕተ እድ  - የእጅ ጣት
ይቀጥላል.......

ምንጭ :ጉባዔ አርድእት

Monday, May 4, 2020

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


"ወዳጄ ሆይ! እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ መስጠትን እንድትለማመድ ነው፡፡ ዛሬ በነዳያኑ አድሮ የሚለምንህ ለኋለኛይቱ ቀን ስንቅ እንዲያስቀምጥልህ ወድዶ ነው፡፡ ታድያ ንጉሥ ወደ ቤቱ መጥቶ የሚያባርር ሰው እንደምን ያለ ጎስቋላ ሰው ነው? እንግዲያውስ ነዳያንን ስታይ ወደ አንተ የመጣው ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ እንጂ ሰው አይደለምና አትግፋው፡፡ በረከትህንም ከቤትህ አውጥተህ አትሸኘው፡፡"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"አንድ ነዳይ አጥብቆ እየለመነህ በቸልታ ትተኸው ስትሔድ እግዚአብሔርን አጥብቀህ በምትለምን ጊዜ ቢተውህ የሚሰማህን አስብ።"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"እንደ ሰውነታችን ዕለት ዕለት እንበድላለን፡፡ በጥምቀት ያገኘነውን ልጅነት እናቆሽሸዋለን፡፡ አዲሱን ሰውነታችን ብሉይ እናደርገዋለን፡፡ ነገር ግን ይህን ዕለት ዕለት ማደስ ይቻላል፡፡ አንድ ቤት እያረጀ ቢሄድ እንደ አዲስ እንሠራዋለን፡፡ ክዳኑን፣ ቀለሙን፣ ምንጣፉን እድሳት እናደርግለታለን፡፡ እኛም በኃጢአት ባረጀው ሰውነታችን ላይ እንዲህ ልናደርግ ይገባናል በንስሐ፡፡"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል፡፡"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ



የቅዱስ ያሬድ የዜማ ምልክቶች

የቅዱስ ያሬድ የዜማ ምልክቶችና ሚስጥራቸው!
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያናችን ካፈራቻቸውና ለአገርና ለቤተክርስቲያን ዘመን ተሻጋሪ ጉልህ አስተዋጽኦ ካበረከቱት ሊቃውንት መካከል አንደኛውና በቀዳሚነት የሚጠቀስ አባት ነው። ቅዱስ ያሬድ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበትን የዜማ ስልት ያረቀቀ ሊቅ ሲሆን እነዚህ የዜማ ሥልቶችም ከሰማይ የተቀበላቸው ሲሆኑ ግእዝ፣ ዕዝልና አራራይ በመባል ይታወቃሉ። ቅዱስ ያሬድ እነሞዛርትና ቤትሆቭን ከመነሣታቸው ከሺህ ዓመታት አስቀድሞ ተፈጥሯዊ ዜማን በምልክት የገለጸና የዜማ ሥልቶችን በሥርዓት ያረቀቀ ዕውቅ የዜማ ሊቅ ነው።
ከዜማ ስልቶቹ በተጨማሪ ቅዱስ ያሬድ የተለያዩ መጽሐፍትን በመድረስ ለቤተክርስቲያን አበርክቷል። ከደረሳቸው መጽሐፍት መካከልም ድጓ፣ ፆመ ድጓ፣ ዝማሬ መዋሥዕት ወዘተ ይገኙበታል። ሉቁ በድጓ መጽሐፉ ላይ የዐቢይ ፆም ሳምንታትን የየራሳቸው ስያሜ ሰጥቷቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ጸዋትወ መከራ ለማሰብ ስምንቱን የዜማምልክቶች በመጽሐፎቹ ላይ አስቀምጧልናል። እነዚህ የዜማ ምልክቶች በቁጥር ስምንት የሆኑበተሰ ዐቢይ ምክንያት ስምንቱ ማኅበረ አይሁድ ተባብረውና መክረው በብዙ ስቃይ ጌታችንን መስቀላቸውና መግደላቸውን ለማሰብ ነው። እነዚህ ማኅበረ አይሁድ የሚባሉትም
፩] ጸሐፍት ፈሪሳዊያን
፪] ሰዱቃውያን
፫] ረበናት (መምህራነ አይሁድ)
፬] መገብተ ምኩራብ (የምኩራብ ሹማምንት)
፭] መላሕቅተ ሕዝብ (የሕዝብ ሽማግሌዎች)
፮] ሊቃነ ካህናት
፯] ኃጥአን እና
፰] መጻብሓን (ቀራጮች) ናቸው።
ቅዱስ ያሬድ ለቤተክርስቲያናችን ያበረከታቸው ስምንቱ የዜማ ምልክቶችም
፩} ይዘት - በአይሁድ ጭፍሮች ለመያዙ (ማቴ 26:50)
፪} ሂደት - ታሥሮ ለመጐተቱ
፫} ጭረት - ለግርፋቱ ሰምበር
፬} ድፋት - የእሾህ አክሊል ለመድፋቱ
፭} ደረት - መስቀል ላይ አንጋለው ደረቱ ላይ ረግጠው ስለመቸንከራቸው
፮} ርክርክ - ስለደሙ ነጠብጣብና አወራረድ
፯} ቁርጥ - በጦር ተወግቶ ፈጽሞ መሞቱ ስለመታወቁ ወይም አይሁዳውያን ጌታችንን ለመስቀል ቁረሰጥ ውሳኔ ስለመወሰናቸው
፰} ቅንዓት - በቅንዓተ አይሁድ ለመገደሉ ምልክቶችና ማስታወሻ ምሳሌዎች ናቸው!
ይሁን እንጂ ቅዱስ ያሬድ ከእነሞዛርትና ቤትሆቨን የቀደመ ሊቅ ሆኖ ሳለ ዛሬም ድረስ ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና እንዲኖር ስላልተሠራ በቤተክርስቲያን ሊቃውንት ዘንድ ብቻ ተወስኖ እንዲቀር ሆኗል። የቅዱስ ያሬድን ሥራዎች ለዓለም በመመስከርና ሊቁን በማስተዋወቅ የኢትዮጵያን ልዕልና ዓለም እንዲያውቀው ለማድረግ እያንዳንዳችን የበኩላችንን መወጣት ይኖርብናል። ይህን ማድረግ የምንችለው ደግሞ አስቀድመን እኛ ሊቁንና ሥራዎቹን ማወቅ ስንችል ነውና ሊቁን እንወቀው። የልዑል እግዚአብሔር ቸርነትና የቅዱስ ያሬድ በረከት ከኹላችን ጋር ይሁን አሜን።
© ዳንኤል ገብረማርያም 

Saturday, May 2, 2020

ተክለ ሃይማኖት

መነነቶ ወኅደገቶ
ለተክለሃይማኖት አብ ጽኑዓ ሃይማኖት መሐላ
ብእሲት እግሩ ዘዓቢይ ኅይላ
ወኢፈቀደት ነቢረ ውሳጤ ቀዊም መርጡላ
ስድስተ አክናፈ ደቂቀ ተድላ
በላዕሌየ ወለደ ብሂላ

ትርጉም: ሃይሏ ትልቅ የሆነ እግሩ/ሴት የሀይማኖት መሃላን ያጠና ተክለሃይማኖትን ናቀችውና ተወችው። ስድስት ክንፎችን/የምቾት ልጆችንም በላዬ ወለደ ብላ በመቆሚያ ቤቷ ውስጥ መኖርን አልወደደችም።

ትንታኔ፡ የጎልማሳ ሚስት ባልዋ በላይዋ ላይ ከሌላ ሴት ልጅ ከወለደ ትታው እንደምትለየው ሁሉ ጻድቅ ተክለሃይማኖትም ሰባት ዓመት ቆመው  ሲጸልዩ አንድ እግራቸው ተሰብሮ ስድስት የጸጋ ክንፎች አገኙ ይላሉ ባለቅኔው።

Friday, May 1, 2020

ግዕዝ ይማሩ

ክፍል አንድ
 የ"ሀ"ን ነጠላ ግስ ዘርና ነባር/Dictionary  የሚያሳየውን የ"ሀ"ነጠላ ግስ እንመለከታለን!!!
መልካም ጥናት!!!
ግዕዝ          ትርጉም
ሎሀ       -        ጻፈ
መርሐ    -        መራ
ሰርሐ     -      አቀና፡አከናወነ
ሰብሐ    -            አመሠገነ
 ሰብሐ   -           ሰባ
በዝሐ    -            በዛ
ጸንሐ     -     ቆየ፡ አበደ
ጼሐ      -        ጠረገ
ፈልሐ    -       ፈላ
ፈርሐ     -       ፈራ
ፈትሐ     -       ፈረደ
በጽሐ     -       ደረሰ
ተግሀ     -       ተጋ
ተፈስሀ   -      ደስ አለው
ነስሀ      -      ተመለሰ
ነቅሐ     -      ነቃ ፡ ነዳ
ነብሐ/ከልሐ  -       ጮኸ
ነግሀ/ጎሀ      -      ነጋ
ነጽሐ             -     ንጹሕ ሆነ
ኖኀ               -      ረዘመ
ለብሐ/ጠብሐ   -      አረደ
ጸርኸ                -     ጮኸ
ናሁ                   -     አሁን
በሊህ                -       ስለት
አምኀ                -     እጅ ነሳ
ብዙሕ               -       ብዙ
ወርሀ                -   ጨረቃ/ብርሃን
አንቆቅኆ           - እንቁላል
ኦሆ                  -   እሽ/በጀ

ምንጭ:ጉባዔ አርድእት

ይቆየን....

የድንግል ማርያም ምልጃ በቅኔ

ተዘከር ወልድ ፍተ ርህራሄከ እክል
እስመ ቅድመ ገጽከ ቆመት ሰዓሊተ ምህረት ድንግል
ትርጉም:
ወልድ የርህራሄ እህል ቁራሽን ተዘከር(አስብ)
ምህረትን ለማኝ በፊትህ ቆማለችና
ትንታኔ:
እንጀራ የምትለምን ሴት ቁራሽ ተዘከሯት እንደሚባል ወልድ ሆይ ለእናትህ የሰጠሃትን ቃልኪዳን አስበህ በፊትህ ቆማ ስትማልድ ራራ ይላሉ ባለቅኔው።
(ባለቅኔው )አለቃ ወልደማርያም ሀብቱ



ቅዱስ ጊዮርጊስ

ሚያዝያ 23 እረፍቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ

ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ #በጥር 20 ቀን በ277 ዓ.ም ተወለደ። ሀገሩ ፍልስጤም ሲሆን ልዩ ስሟ ልዳ ይባላል። ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ፣ ብሩህ፣ ሐረገወይን፣ ፀሐይ ማለት ነው። አባቱ ዞሮንቶስ የተባለ የልዳ መኳንንት እናቱ ቴዎብስታ ትባላለች። ማርታና እስያ የሚባሉ እህቶች ነበሩት። #10 ዓመት ሲሞላው አባቱ ስለሞተ ሌላ ደግ ክርስቲያናዊ መስፍን ከቤቱ ወስዶ አሳደገው። በጦር ኃይልም አሠለጠነው። ሃያ አመት ሲሞላው መስፍኑ የ15 ዓመት ቆንጆ ልጅ ነበረችውና እርሷን አግብቶ ሀብቴን ወርሶ ይኑር ብሎ ድግስ #ሲያስደግስ ጌታ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዚህ አላጨውምና የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ። እርሱም ኀዘኑን ጨርሶ ወደ ቤሩት ሄደ።
#በቤሩት ደራጎንን ያመልኩና ሴት ልጃቸውን ይገብሩለት ነበርና በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ህዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል። ወደፋርስ ቢመለስ ዱድያኖስ ሰባ ነገሥታት ሰብስቦ ሰባ ጣዖታት አቁሞ ሲሰግድ ሲያሰግድ ቢያገኛቸው ለሃይማኖቱ ቀናዒ ነውና ከቤተመንግስቱ ገብቶ “እኔ ክርስቲያን ነኝ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ” አለው። እርሱም ማንነቱን ከተረዳ በኋላ “አንተማ የኛ ነህ #በ10 አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ” አለው። ቅዱስ ጊዮርጊስም “ሹመት ሽልማትህ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክድም” አለ። በዚህ ጊዜ እጅግ ተናዶ መከራን አጸናበት እርሱ ግን “ይህን #ከሀዲ እስካሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰድ”በማለት እግዚአብሔርን የለመነና እንደጸሎቱ የተደረገለት። በእምነቱም ጽናት የሰው ልጅ ሊሸከም የማይችለውን መከራ የተቀበለ ቅዱስ አባት ነው።
ከእነዚህም መከራዎች ውስጥ፡-
1. #በእንጨት አስቀቅሎ ሥጋውን በመቃን አስፈተተው፣ ረጃጅም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማ አጫምቶት ሂድ አለው። ቅዱስ ሚካኤልን ልኮለት ፈውሶታል። በሰባ (70) ችንካር አስቸንክሮ በእሳት አስተኩሶ አናቱን በመዶሻ አስቀጥቅጦ በሆዱ ላይ የደንጊያ ምሰሶ አሳስሮ እንዲያንከባልሉት አደረገ። ሥጋውን በመጋዝ አስተልትሎ ጨው ነስንሶበት ሥጋው ተቆራርጦ ወደቀ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት በእጁ ዳስሶ “ገና 6 ዓመት ለስሜ ትጋደላለህ፣ 3 ጊዜ ትሞታለህ፣ በ4ኛው ታርፋለህ።” አለው።
2. #ዱድያኖስ ደንግጦ “የሚያሸንፍልኝ ቢኖር ወርቅ እሰጠዋለሁ” ቢል አትናስዮስ የተባለ መሰርይ ከንጉሱ ላምን በጆሮዋ ሲያንሾካሹክባት ለሁለት ተሰንጥቃ ገድሏት ፈቃድን ተቀበለ። ሆድ በጥብጦ አንጀት ቆራርጦ የሚገድል መርዝ ቀምሞ አስማተ ሰይጣን ደግሞ ሰጠው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ ቢጠጣው እንደ ጨረቃ ደምቆ እንደ አበባ አሸብርቆ ተገኝቷል። ጠንቋዩም ማረኝ ብሎት ከእግሩ ወደቀ። መመለሱን አይቶ የቆመባትን መሬት በእግሩ ረግጦ ውሃን አፍልቆ ወደ ጌታችን ቢያመለክት ሐዋርያው ቶማስ በመንፈስ መጥቶ አጥምቆት ጥር 23 ቀን አንገቱን ለሰይፍ ሰጥቶ በሰማዕትነት አርፏል። እሱን ግን በመንኮራኩር አስፈጭቶ ከትልቅ ጉድጓድ ጥሎት ደንጊያ ዘግቶበት አትሞበት ሄዷል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተፈጨውን ሥጋ በእጁ ዳስሶ መንፈሱን መልሶ አንስቶታል፤ ተመልሶም “አምላኬ ከሞት አዳነኝ” ብሏቸዋል።
3. #በብረት አልጋ አስቸንክሮ ከበታቹ እሳት አንድዶበታል። እሳቱም ደሙ ሲንጠባጠብ ጠፍቷል። ዱድያኖስ “ኢየሱስ አምላክ መሆኑን አሳየኝ” ቢለው የለመለሙትን ዕፅ አድርቆ፣ የደረቁትን አለምልሞ፣ ከሞቱ 430 ዓመት የሆናቸውን ሙታንን አስነስሰቶ አሳይቶታል። ነገር ግን ልቡ ክፉ ነውና በረሀብና በጽም ይሙት ብሎ ምንም ከሌላት መበለት ቤት አሳስሮታል። እርሷም የሚቀመስ ስትፈልግ ቤቷን በእህል አትረፍርፎ የታሰረበት ግንድ አፍርቶ ልጇ ጆሮው የማይሰማ ነበርና ፈውሶላት መበለቲቷን ከነልጆቿ አጥምቆ ቅዱስ ሚካኤል ከእስራቱ ፈትቶት ተመልሷል። ዳግም በመንኩራኩር ፈጭታችሁ ደብረ ይድራስ ወስዳችሁ ዝሩት ብሎ አስፈጭቶ ሥጋውን ቢዘሩት ሥጋው ያረፈበት ሳር፣ ቅጠሉ፣ ደንጊያው፣ እንጨቱ ሁሉ “ጊዮርጊስ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር፣ ጊዮርጊስ ሰማዕቱ ለእግዚአብሔር፣” እያሉ አመስግነዋል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሦስተኛ ጊዜ ከሞት አስነስቶታል። ሔዶም “አምላኬ ከሞት አዳነኝ” አላቸው። ጭፍሮቹ ደንግጸው ከእግሩ ስር ወደቁ። ከመሬት ውሃ አመንጭቶ ቅዱስ ዮሐንስ አጥምቋቸዋል።
 4. “#ንጉሡ ልሹምህ ለአጵሎን ስገድ” ብሎ ቢለምነው እሺ ብሎ ገብቶ ሲጸልይ የንጉሱ ሚስት እለእስክንድርያ “ምን እያልክ ነው?” ብትለው አስተምሯት አሳምኗታል። ሲነጋ ንጉሱ በአዋጅ ህዝብን አሰብስቦ “ጊዮርጊስ ለጣዖቴ ሊሰግድ ነው’ ብሎ በተሰበሰበ ህዝብ መካከል አንድን ብላቴና (የመበለቷን ልጅ) “የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ ጊዮርጊስ ይጠራሃል” በል ብሎ ወደጣዖቱ ቢልከው ጣዖቱ ላይ ያደረው ሰይጣን እየጮኸ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለበት ቦታ መጣ፤ አምላክ አለመሆኑን አናዞት መሬት ተከፍታ እንድትውጠው አደረገ። ብዙ ሰዎች ይህንን ተዓምር አይተው አመኑ። ንጉሱን ሚስቱ እንዲመለስ ብትነግረው በአደባባይ አሰቅሎ አሰይፏት ሞታለች ደሟን ጥምቀት አድርጎላት ሰማዕት ሆናለች። በመጨረሻም በሰይፍ እንዲመተር አስደረገ። ቅዱስ ጊዮርጊስም ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃልኪዳን ተገብቶለት በ27 ዓመቱ በሚያዝያ 23 ሰማዕት ሆኗል። አንገቱ ሲቆረጥም ውሃ፣ ደም እና ወተት ወጥቷል።
ከሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት በረከት ይክፈለን!!!
(ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ)

Thursday, April 30, 2020

ዜና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን መንግስት በመስቀል አደባባይና ጃንሜዳ እያከናወነ ያለው ተግባር መብቴን ጥሷል አለች
++++++++++++
ዋዜማ ራዲዮ- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀትና የመስቀል ዳመራ የሚከበሩበት መስቀል አደባባይና ጃንሜዳ ላይ መንግስት ፈቃደኝቴን ሳይጠይቅ ሳያማክረኝ በወሰዳቸው እርምጃዎች “የባለቤትነት” መብቴን ተጋፍቷል ለዚህም ማብራሪያ እንዲሰጠኝ ስትል ጠየቀች።
ለዋዜማ ራዲዮ የደረሰው ከቤተ ክርስቲያኒቱ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የተላከው ደብዳቤም ይህንኑ ይገልጻል።
በአቡነ ያሬድ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚለው እነዚህ ከመንፈሳዊና ባህላዊ እሴቶች በተጨማሪ ለሀገሪቱ ትልቅ የገቢ ምንጭ በመሆን የታወቁትን በአላት ማክበሪያ ቦታዎችን የበለጠ በመንከባከብና እሴቶቻቸውን በመጠበቅ የቱሪስት ፍሰቱ እንዲጨምርና የሀገሪቱ ገቢ አድጎ የህዝቡን ተጠቃሚነት በበለጠ ሁኔታ እንዲረጋገጥ ለቦታዎቹ ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ በማድረግ ፈንታ ይባስ ብሎ የበአለ ጥምቀቱን ቦታ ለገበያ ማእከልነት እንዲሁም የበአለ መስቀል ማክበሪያውን ቦታ ደግሞ “ምንነቱ ላልታወቀ” ፕሮጀክት እንዲውል ሲያደርግ የበአሉም ሆነ የቦታው ጥንተ ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያኒቱ ሳትጠየቅና በጉዳዩ ላይ ሳታምንበት ግልፅነት በጎደለው ሁኔታ ወደ ትግበራ በመገባቱ ቤተ ክርስቲያኒቱን በእጅጉ ያሳዘነ ተግባር ነው።
እንዲሁም በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታና ቁጣን በማስከተሉ የመልካም አስተዳደር ችግር እየፈጠረብን ነውም ይላል ደብዳቤው። ደብዳቤው አክሎም የከንቲባ ጽህፈት ቤት የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት በማስገባትና ልዩ ትኩረት በመስጠት በጉዳዩ ላይ ተገቢውም አፋጣኝ ምላሽ ይስጠን ሲል ይጠይቃል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ያግዘኛል በሚል ፒያሳ ያለውን የአትክልት ተራ መጨናነቅ ለመቀነስ ገበያውን ወደ ጃንሜዳ መቀየሩ ይታወቃል። ከቀናት በፊት ደግሞ አዲስ አበባን የማስዋብ እቅድ አካል ነው የተባለ የመስቀል አደባባይ ማዘጋጃ ቤት ፕሮጀክትን ለመስራት የመስቀል አደባባይን መቆፈር ተጀምሯል።የዋዜማ ሪፖርተር ስፍራው ላይ ተገኝቶ እንደተመለከተው የቁፋሮው ስራ እጅጉን እየተፋጠነ ነው።
በቤተክርስቲያኒቱ ለጉዳዩ ከፍተኛ ቅርበት ያላቸው ግለሰብ ከዋዜማ ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ መንግስት በፈጸመው ድርጊት የቤተ ክርስቲያኒቷን ህጋዊ መብት ተጋፍቷል ብለውናል። የጃን ሜዳውን እና የመስቀል አደባባዩ ጉዳይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ስጋት መፍጠሩን ያነሳሉ። የጃን ሜዳውን የአትክልት ግብይት ቦታ መሆኑን በተመለከተ ፣ መንግስት ይህን ያደረገው የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ነው መባሉ በራሱ ችግር ባይሆንም ፣ እንደተባለው ጃን ሜዳ ለገበያ ቦታነት የተፈለገው በጊዜያዊነትና የወረርሽኙ ጊዜ እስኪያልፍ ለመሆኑ ምን ማረጋጫ አለ ? የሚል ጥያቄ በቤተ ክርስቲያኒቱ ዘንድ አለ ይላሉ። አሁን ጊዜያዊ ተብሎ ቀጣይ የሚኖር አስተዳደር ቦታውን በቋነሚት ወደ ግብይት ቦታ ልቀይር አለማለቱ በምን ይታወቃል? ይህም በቀጣይ ግጭትና አላስፈላጊ ንትርክ ሊያስከትል ስለሚችል ከተማ አስተዳደሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሳያማክርና አስተያየቷን ሳይቀበል : ይሁንታንም ሳያገኝ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰበትን ህጋዊ መሰረት እንዲያስረዳም ነው ቤተ ክርስቲያን የምትፈልገው ብለውናል ምንጫችን።
የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ቅሬታ እንደገባትም ጠቁመውናል። የመስቀል በአል በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ላይ ሲሰፍር ያለው አረደዳድ የተመዘገበው በዓሉም ብቻ ሳይሆን የዳመራ ስነስርአቱና የሚከበርበት ቦታ እንደመሆኑ ታዲያ የአዲስ አባበ ከተማ አስተዳደር የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክትን አስመልክቶ ይፋ ያደረገው በቪድዮ የተደገፈ ዲዛይን ለቤተ ክርስቲያኒቱ እንግዳ ነገር ሆኖባታልም ።
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት ግለሰብ እንዳሉን በቪድዮ የተደገፈው ዲዛይን ደመራው የሚተከልበትን ቦታ እና የተለያዩ መንፈሳዊ ትርኢቶች የሚታዩባቸው ስፍራዎች ላይ ዛፍ ተተክሎበት ስለሚያሳይ የመስቀል ደመራ እንዴት እንዲከበር ታስቦ ዲዛይኑ እንደተሰራም ግራ አጋቢ በመሆኑ ለቤተ ክርሰቲያኗ ማብራሪያ አስፈጓታል።

ጻድቁ ተክለሃይማኖት በጸሎት እግሩ እንደተሰበረች በቅኔ


መነነቶ ወኅደገቶ
ለተክለሃይማኖት አብ ጽኑዓ ሃይማኖት መሐላ
ብእሲት እግሩ ዘዓቢይ ኅይላ
ወኢፈቀደት ነቢረ ውሳጤ ቀዊም መርጡላ
ስድስተ አክናፈ ደቂቀ ተድላ
በላዕሌየ ወለደ ብሂላ
#ትርጉም: ሃይሏ ትልቅ የሆነ እግሩ/ሴት የሀይማኖት መሃላን ያጠና ተክለሃይማኖትን ናቀችውና ተወችው። ስድስት ክንፎችን/የምቾት ልጆችንም በላዬ ወለደ ብላ በመቆሚያ ቤቷ ውስጥ መኖርን አልወደደችም።
#ትንታኔ፡ የጎልማሳ ሚስት ባልዋ በላይዋ ላይ ከሌላ ሴት ልጅ ከወለደ ትታው እንደምትለየው ሁሉ ጻድቅ ተክለሃይማኖትም ሰባት ዓመት ቆመው  ሲጸልዩ አንድ እግራቸው ተሰብሮ ስድስት የጸጋ ክንፎች አገኙ ይላሉ ባለቅኔው።
ባለቅኔው መሪጌታ ያሬድ ዘቂርቆስ

Wednesday, April 29, 2020

ምክረ አበው


"በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው"ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ
"ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል" ቅዱስ ቆጵሮሳዊ
"የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው" ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ
"መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም" ቅዱስ ባስልዮስ
"ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር" ሊቁ ጠርጡለስ

Monday, April 27, 2020

ቃለ እግዚአብሔር

++ እንዴት ወድቀን እንዴት ተነሣን? ++
እንዴት ወድቀን እንዴት ተነሳን በዲ.ን ሔኖክ ኃይሌ
ኦሪት ዘፍጥረት ስለሰው ልጅ ውድቀት ሲናገር ዕባብና ሔዋን ያደረጉትን ቃለ ምልልስና በዕባብ ምክር ሠጪነት የሰው ልጅ እንዴት ከገነት እንደተባረረና ጸጋውን እንደተገፈፈ ያስረዳል፡፡

    ይህንን የዕባብና የሔዋን ቃለ ምልልስን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብናወጣው ወይም ኦሪት ዘፍጥረት የአዳምና ሔዋንን ከገነት መባረር ብቻ የሚናገር ቢሆን ኖሮ ‹ምን አጥፍተው ነው የተባረሩት?› ወደሚል ግራ መጋባት ውስጥ እንገባ ነበር፡፡

    ወዳጄ የዕባብና ሔዋንን ቃለ ምልልስ መስማት ሳይችል  የአዳምና ሔዋንን ከገነት የመባረር ታሪክ ለመረዳት የሚችል እንደሌለ ሁሉ የእመቤታችንንና የቅዱስ ገብርኤልን ቃለ ምልልስ ሳያነብ የሰው ልጅን ወደ ገነት የመግባትና የመዳን ታሪክ ለመረዳት የሚችል ሰው ማንም የለም፡፡

 
ቅዱስ ጳውሎስ በአዳምና በክርስቶስ ተምሳሌት (Christ-Adam analogy) አድርጎ ጻፈ::  ክርስቶስን ‹ኋለኛው አዳም› ብሎ ጠርቶታል፡፡ (1ቆሮ. 15፡45) አዳምንም ‹አዳም ይመጣ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነው› በማለት የክርስቶስ ምሳሌ እንደሆነ አስረድቷል፡፡ (ሮሜ. 5፡14) የሰው ልጅ ተፈጥሮ ታሪክ የተጀመረው ከአዳም ታሪክ እንደነበር የሰው ልጅ አዲሱ ተፈጥሮ ታሪክም የተጀመረው በዳግም ፍጥረት (Recaptulation) በተፈጠርንባት በቀራንዮ ነው፡፡

ይህም ንጽጽርም  በኁዋላ ዘመን ለተነሡ እንደሰማዕቱ ዮስጦስና እንደ ያዕቆብ ዘሥሩግ ያሉ ሊቃውንት የማርያምና ሔዋን ተምሳሌትን (Mary eve analogy) እንዲያመሠጥሩ መነሻ ሆናቸው:: ያነጻጸሩት ሔዋንን ከማርያም ብቻ ሳይሆን እንዴት ወደቅን እንዴት ተነሣን የሚለውን ነው::

ሔዋን ለውድቀታችን መነሻ ነበረች ማርያም ግን ለመነሳታችን ምክንያት ሆነች:: ሔዋንን ሰይጣን በዕባብ ተመስሎ አነጋገራት:: ማርያምን ግን እግዚአብሔር በገብርኤል ሆኖ አነጋገራት:: ሔዋን የዕባቡን ቃል በመስማትዋ ከገነት ወጣን : ማርያም የገብርኤልን ቃል በመስማትዋ ወደ ገነት መለሰችን::

የዕባብና የሔዋንን ቃለ ምልልስ በቁጭት እናነበዋለን:: የድንግልና የገብርኤልን ምልልስ ግን በደስታ እንጸልየዋለን:: ያ ቃለ ምልልስ እኛን ወደ ሕይወት የመለሰ ቃለ ምልልስ ነው:: የ15 ዓመትዋ ብላቴና ማርያም ምድራዊያንን ሁሉ ወክላ ከሰማያዊው መልእክተኛ ጋር ተነጋግራ ዕርቃናችንን አለበሰችን:: የድሆች ልጅ የሆነችው ብላቴና የመላእክትን አለቃ በጥያቄ አስጨንቃ መርምራ ከጭንቃችን ገላገለችን::

ሔዋን የዕባብን ምክር ሳትመረምር ተቀበለች:: ድንግል ማርያም ግን የገብርኤልን ብሥራት መረመረች:: ለሔዋን ዲያቢሎስ "እግዚእብሔር እንደርሱ እንዳትሆኑ ብሎ ከለለላችሁ" ብሎ ከፈጣሪ አጣላቸው:: ሔዋን ሁሉን አዋቂ ለመሆን ቸኩላ ከባልዋ ጋር ፈጠነች:: ድንግል ማርያም ግን ሁሉን አዋቂ ልሁን አላለችም :: "ወንድ ስለማላውቅ እንዴት ይሆንልኛል? ብላ ጠየቀች : ሔዋን አምላክ ለመሆን ተታለለች:: ትሕትና የሞላባት ድንግል ግን "እነሆኝ የጌታ ባሪያው ነኝ" ብላ ተቀበለች::

ይህች ድንግል ገብርኤልን ሰምታ የሕይወትን ዛፍ አበላችን:: ይህች ድንግል ይሁንልኝ በማለትዋ የተጠመቅን ሁላችን ክርስቶስን ለበስን:: በእርስዋ ይሁንልኝ ማለት ኪሩብ ሰይፉን ጣለ : ከጥበቃም ተገላገለ:: እኛም ከዕፀ ሕይወት እንበላ ዘንድ ታደልን::

ብዙ ሰው " ሔዋን ለመውደቃችን ምክንያት ናት " ሲባል ይስማማል:: ድንግል ማርያም ግን ለመዳናችን ምክንያት ሆነች የሚለውን ግን አንዳንዶች ለመቀበል ይቸገራሉ:: ሔዋን ለመውደቃችን ካደረገችው ይልቅ ድንግል ማርያም ለመነሣታችን ያደረገችው ይበልጣል!

የድኅነታችን መጀመሪያ የሆነችውን ይህችን ድንግል ክብርዋን በሕሊናችን እንሳለው:: እሳታዊ መልአክ ቆሞ የዘመረላት ድንግል : አባትዋ ዳዊት ከሩቅ ሆኖ እያያት "ልጄ ሆይ ስሚ እዪም ጆሮሽን እዘንብዪ" እያለ የገብርኤልን ቃል እንድትሰማና ከሲኦል እንድታወጣው የሚማጸናትን ድንግል : ወንድምዋ ሰሎሞን "እኅቴ ሙሽራ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም" እያለ የቀረበላትን 'የተባረክሽ ነሽ' የሚል ምስጋና እንድትቀበል የሚዘምርላትን :  በእጆችዋ ሐርና ወርቅን : በማኅጸንዋ ሰውና አምላክን : በመውለድዋ ሰውና መላእክትን አስማምታ የፈተለችና ያዋሐደችዋን ይህች ድንግል እስቲ ለአፍታ እናስባት:: የባቢሎንን ሰባት እጥፍ የነደደ እሳት ያቀዘቀዘው ገብርኤል በፊትዋ በትሕትና አደግድጎ የቆመላትና ዘካርያስን ዲዳ ትሆናለህ ባለበት አንደበቱ "አንቺ የተባረክሽ ነሽ " እያለ የሚማጸናትን የዐሥራ አምስት ዓመት ብላቴና እስቲ እናስባት! ዓላማ ይዞ እንደተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ይህች ማናት?

ሽማግሌ አባትዋን ቅጠል ከለበሰበት ዛፍ አውጥታ ልጅዋን ሸማ አድርጋ ያለበሰች : እናትዋን ሔዋንንም የሚጎዳ ማሠሪያዋን ፈትታ ቁስልዋን ያከመች የሔዋን መድኃኒት ይህች ድንግል ማን ናት? የእርስዋን ክብር በኃጢአተኛ ብዕር እንደምን እጽፈዋለሁ?
ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ያለውን ብዬ ብዘጋው ይሻለኛል
"የድንግል ማርያምን ክብር ከመግለጽ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 21 2012
አዲስ አበባ

Sunday, April 26, 2020

ፎቶ ጋለሪ

ይዘጋጃል…

ቅዱስ ያሬድ

ኢትየጵያዊዉ ቅዱስ ያሬድ ሚያዝያ 5 ቀን 505 ዓ/ም በአክሱም ከተማ ተወለደ፡፡እናቱ ታዉክሊያ/ክርስቲና/አባቱ ደግሞ ይስሐቅ/አብድዩ/ይባላሉ፡፡አባቱ የ አክሱም ጽዮን ቄሰ ገበዝ ነበር፡፡

በዓላት

በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።ኢሳ.56:5
የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው።ምሳ 107 እግዚአብሄር ለቅዱሳን በቸርነቱ ከሰጣቸው በረከት ለመሳተፍ መታሰቢያቸውን ማድረግ የግድ ነውእናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።”/ማቴ 1040-46/ ይላልና ይህም የተባለው በነብያት፣ በጻድቃንና በሌሎችም ቅዱሳን ስም መታሰቢያ ማድረግ እንደሚገባ ለመግለጽ ነው።እንደሚገባት በዓላትን እና ንዑስ በዓላትን ሙሉ በሙሉ ሳናካትት በከፊል ዓመታዊ በዓላትን እና ወርሃዊ በዓላትን ስንክሳር እና ገድላትን በማንበብ በጦማራችን አቅርበንሎታል፡፡ ለወደፊትም ስራቸውን በተቻለ እናቀርባለን::ዓመታዊ በዓላት
መስከረም 1. ቅዱስ ራጉኤል (ርእስ አውደ ዓመት/
መስከረም 2. ቅዱስ ዮሀንስ /አንገቱ የተቆረጠበት ቀን/
መስከረም 10. ፀደኒያ ማርያም
መስከረም 15 ቅዱስ እስጢፋኖስ(የተሾመበት) (ይህ በዓል ከመስቀል በዓል ጋር የሚታሰብ ነው)
መስከረም 17 ቅዱስ እስጢፋኖስ /በዓለ መስቀል/
መስከረም 21. መናገሻ ማርያም ፡ግሼን ማርያም ፡እንጦጦ ማርያም
መስከረም 29. ቅድስት አርሴማ
ጥቅምት 5. አቡነ ገብረመንፈስ
ጥቅምት 9. አባ አትናስዮስ(እረፍቱ)
ጥቅምት 12.አባ ዲሜጥሮስ(እረፍቱ)
ጥቅምት 13.አባ ዘካርያስ(እረፍቱ)
ጥቅምት 14. አቡነ አረጋዊ (የተሰወሩበት) በገብረክርስቶስ(እረፍቱ) ኢትዮጰያዊውን ጀንደረባ ያጠመቀውን ዲያቆኑ ፊሊጶስ (እረፍቱ)
ጥቅምት 17. ቅዱስ እስጢፋኖስ(የተሸመበት)
ጥቅምት 20. ዮሐንስ ሐፂር(እረፍቱ)
ጥቅምት 21.ነቢየ እግዚአብሔር ኢዩኤል (እረፍቱ)
ጥቅምት 22. ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ (እረፍቱ) ጥቅምት 25 አቡነ ሀቢብ አረፈ
ጥቅምት 27. መድሐኔአለም: አባ መብዓ ፅዮን (እረፍታቸው)
2
ጥቅምት 8. ቅዱስ አማኑኤል
ጥቅምት 30. ቅዱስ ማርቆስ /ልደቱ/
ህዳር 6. ቁስቋም ማርያም እመቤታችን ስደቷን ጨርሳ የገባችበት
ህዳር 7. ሕንጻ ቤቱ ለጊዮርጊስ/ አጥንቱ ተሰብስቦ መቃብር ቤት የገባበት/
ህዳር 8. በዓል አርባዕቱ እንስሳ /ክሩቤል ሱራፌል/አባኪሮስ
ህዳር 11. ዕረፍተ ቅድስት ሀና
ህዳር 12. ቅዱስ ሚካኤል፡
ህዳር 13. እግዚአብሔር አብ/የአእላፍ መላእክት ቀን
ህዳር 14. አባ ዳንኤል እረፍቱ
ህዳር 15. ቅዱስ ሚናስ እረፍቱ
ህዳር 18. ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ እረፍቱ 12 ሐዋርያት አንዱ
ህዳር 21. ፅዮን ማርያም/የእመቤታችን በዓል/
ህዳር 24. ሀያአራቱ ካህናተ ሰማይ /ደብረ ሊባኖስ/
ህዳር 25. ቅዱስ መርቆሪዎስ ሰማዕቱ /እረፍቱ/
ህዳር 26. አቡነ ሀብተማርያም /ደብረሊባኖስ/ አባ ኢየሱስ ሞአ(እረፍቱ)
ህዳር 27. አባ ተክለሃዋርያት ሐዋርው ቅዱስ ያዕቆብ በሰማዕትነት አረፈ
ህዳር 29. ተፈፃሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ(እረፍቱ)
ታህሳስ 1.ነቢዩ ኤልያስ የተወለደበት ቀን
ታህሳስ 3. በአታ ለማርያም እመቤታችን በሶስት አመቷ ቤተመቅደስ የገባችበት፡ አቡነ ዜና ማርቂስ(እረፍቱ)
ታህሳስ 4. ሐዋርያው እንድርያስ በሰማዕትነት ያረፈበት
ታህሳስ 6. ቅድስት አርሴማ(ቅዳሴ ቤቷ)
ታህሳስ 12. አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
ታህሳስ 13. ቅዱስ ሩፋኤል
ታህሳስ 15. አባ ጎርጎርዮስ (እረፍቱ) ዘሀገረ አርማንያ
ታህሳስ 19. በዓለ ቅዱስ ገብርኤል
ታህሳስ 22. ብስራተ ገብርኤል /እመቤታችን ክርስቶስን እንደምትወልድ ያበሰረበት/
ታህሳስ 24. አቡነ ተክለሀይማኖት /ልደታቸው/
ታህሳስ 28. ቅዱስ አማኑኤል በዓለ ልደት ለእግዚእነ ገና
ታህሳስ 29. ቅዱስ በዓለ ወለድ /ተዘከረ ልደቱ ለእግዚነ/ገና/
ጥር 1. ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሚ ሰማእት (እረፍቱ)
ጥር 4. ቅዱስ ዮሐንስ /ወንጌላዊ/ወልደ ነጎድጓድ
ጥር 6. ኢየሱስ/ግዝረቱ ለእግዚእነ /እየሱስ ገዳም/ ነቢዩ ኤልያስ የተሰወረበት ቀን
ጥር 7. ቅድስት ሥላሴ
ጥር 11. በዓለ ጥምቀት
ጥር 12. በዓለ ቅዱስ ሚካኤል /ቃና ዘገሊላ/
ጥር 13. ቅዱስ ሩፋኤል /የቃና ዘገሊላ በዓል መታሰብያ/
ጥር 14 አቡነ አረጋዊ
ጥር 15. ቅዱስ ቂርቆስ እየሉጣ
ጥር 18. ቅዱስ ጊዮርጊስ /ዝርዎተ አጽሙ/
ጥር 21. የእመቤታችን በዓለ እረፍት
ጥር 22. ቅዱስ ኡራኤል ቃል ኪዳን የተቀበለበትና የተሸመበት ቀን
ጥር 23. ሐዋርያው ጢሞቲዋስ (እረፍቱ)
ጥር 24. አቡነ ተክለሃይማኖት
ጥር 28. ቅዱስ አማኑኤል 5000 ሰዎች ጌታችን ህብስቱን ያበረከተበት
 
የካቲት 3. አባ ያዕቆብ (እረፍቱ)
የካቲት 8. ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ወደ ምኩራብ የገባበት ቀን(የአረጋዊው የስምዖን ታሪክ ልብ የበሉ)
የካቲት 9. አባ በርሱማ (እረፍቱ)
የካቲት 15. ነቢዩ ዘካርያስ (እረፍቱ)
የካቲት 16. ኪዳነምህረት /እመቤታችን ቃልኪዳን የተቀበለችበት/
የካቲት 20. ቅዱስ ፊልጶስ
የካቲት 23. ቅዱስ ጊዮርጊስ
የካቲት 26. ነቢዩ ሆሴዕ (እረፍቱ)
የካቲት 28. ሮማዊው ቅዱስ ቴዌድሮስ(እረፍቱ)
መጋቢት 4. ቅዱስ ጊዮርጊስ /ደብረዘይት/
መጋቢት 3. ተዝካረ ልደቱ ለአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
መጋቢት 10. መስቀሉን ንግስት እሌኒ ቆፍሬ ያገኘችበት ቀን መድሀኔአለም
መጋቢት 15. ቅድስት ሳራ(እረፍቷ)
መጋቢት 22. ጥንተ ሆሳእና
መጋቢት 27. ቸሩ መድሃኒአለም (የጌታችን ጥንተ ስቅለቱ መታሰቢያ)
መጋቢት 29. የበዓለ ወልድ /የጌታችን ጽንሰት/
ሚያዝያ 22. አባ ይስሀቅ(እረፍቱ)
ሚያዝያ 23. የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ እረፍት
ሚያዝያ 27. ምስካየ ሕዙናን /ስደተኛው መድሀኒአለም/
ሚያዝያ 30. ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ያረፈበት ቀን ነው
ግንቦት 1. ልደታ እመቤታችን የተወለደችበት ቀን ነው
ግንቦት 7. ሊቁ አቡነ አትናቲዎስ (እረፍቱ)
ግንቦት 11. ቅዱስ ያሬድ(የተሰወረበት)
ግንቦት 12. አቡነ ተክለሃይማኖት /አፅማቸው የፈለሰበት /ክርስቶስ ሳምራ
ግንቦት 14. አቡነ አረጋዊ፡ ቅዱስ ገብረክርስቶስ
ግንቦት 17. አባ ኤጲፋንዮስ(እረፍቱ)
ግንቦት 21 . እመቤታችን ማርያም /እመቤታችን
ግንቦት 24. ቁስቋም ማርያም /የስደቷ መነሻ/
ግንቦት 28. ቅዱስ አማኑኤል፡ ቅድስት አመተ ክርስቶስ (እረፍቷ)
ሰኔ 8. ከደረቅ ዓለት ላይ ውሃን ያፈለቀበት 33 ከእመቤታችን በዓል አንዱ
ሰኔ 9. ታላቁ ነብይ ሳሙኤል(እረፍቱ)(የሐና ልጅ)
ሰኔ 11.ሰማዕቱ ቅዱስ ገላውድዮስ (እረፍቱ)
ሰኔ 12. ቅዱስ ሚካኤል ባሕራንን ከውሃ ያወጣበት ቀን ነው(አፎምያን ከሰይጣን ያዳነበት) ቅዱስ ላሊበላ(እረፍቱ)
ሰኔ 20.ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን
ሰኔ 21. ጌታችን /የእመቤታችንን ቤት ያነጸበት ቀን ነው፡፡ ግሽን ማርያም በጎልጎታ በጌታችን መቃብር የጸለየችበት
ሰኔ 23.ጠቢቡ ሰሎሞን እረፍቱ
ሰኔ 24. አባ ሙሴ ፀሊም(እረፍቱ)
ሰኔ 25. የዮሴፍ ልጅ ሐዋርው ይሁዳ እረፍቱ
ሰኔ 26. ኢያሱ እረፍቱ
ሰኔ 27. እረፍቱ ለሐናንያ ሐዋርያ
ሰኔ 30. ልደተ ዮሐንስ መጥምቅ
ሐምሌ 2. ሐዋርያው ታዴዎስ(እረፍቱ)
ሐምሌ 3. አባ ቄርሎስ(እረፍቱ)
ሐምሌ 4. ነቢዩ ሶፎንያስ እረፍቱ
ሐምሌ 5. ጴጥሮስና ጳውሎስ እረፍታቸው
ሐምሌ 7. አጋእዝተ ዓለም ስላሴ በአብርሃም ቤት፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እረፍቱ
ሐምሌ 8. አባ ኪሮስ
ሐምሌ 10.ሓዋርያው ናትናኤል እረፍቱ
ሐምሌ 15. ኤፍሬም ሶርያዊው እረፍቱ
ሐምሌ 16. ወንጌላዊው ዮሐንስ እረፍቱ
ሐምሌ 18 .የጻድቁ የዮሴፍ ልጅ ሐዋርያው ያዕቆብ እረፍቱ
ሐምሌ 19. በዓለ ቅዱስ ገብርኤል ቂርቆስና እየሉጣን ከእሳት ያዳነበት ቀን ነው/ቁልቢ ገብርኤል/
ሐምሌ 22. ቅዱስ ኡራኤል ፡አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት የተቀበሉበት
ሐምሌ 23. ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሐምሌ 26. ቅዱስ ዮሴፍ (እረፍቱ) ፡አቡነ ሀብተማርያም ዘደብረሊባኖስ
ሐምሌ 28.ቅድስት መስቀል ክብራ (እረፍቷ)(የቅዱስ ላሊበላ የትዳሩ አጋር)
ሐምሌ 30.ቅድስት ማርያም ክብራ(እረፍቷ)
ነሐሴ 7.ፅንሰታ ለማርያም
ነሐሴ 13. እግዚአብሔር አብ በደብረታቦር ተራራ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱ ለእነ ሙሴና ኤልያስ የገለጸበት ቀን ነው/የቡሄ በዓል/
ነሐሴ 15. ቅድስት እነባመሪና(እረፍቷ)
ነሐሴ 16. ኪዳነምህረት
ነሐሴ 19. አባ መቃርስ የስጋው ፈልሰት
ነሐሴ 21. ጌቴ ሴማኒ ገዳም እመቤታችን (ሰበታ)
ነሐሴ 24. አቡነ ተክለሃይማት እረፍታቸው ፤ክርስቶስ ሳምረ
ነሐሴ 27 ቅዱስ ሱርያል(4 ሊቀ መላእክት)
ነሐሴ 28.አበው አብርሃም ይህሳቅ ያዕቆብ (እረፍታቸው)
ጳጉሜ 2.ሐዋርያው ቲቶ (እረፍቱ)
ጳጉሜ 3. ቅዱስ ሩፋኤል
ጳጉሜ 4.አባ ባይሞን(እረፍቱ)
ወርሃዊ በዓላት
1.
ልደታ፣ዮሐንስ ፣ራጉኤል ፣እዮብ ፣ኤልያስ ሶስና
2.
በርቶሎሚዎስ ፣ጴጥሮስ ፣አባ ጉባ ፣መሪና
3.
በአታ ማርያም ፣ፋኑኤል ፣ዜና ማርቆስ
4.
ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ፣አባ መቃርዎስ፣ አባ አብርሐ
5.
ጴጥሮስና ጳውሎስ ፣ገብረ መንፈስ ቅዱስ
6.
ቁስቋም ፣ኢየሱስ ፣አርሴማ ቅድስት ፣እያሱ
7.
አጋዕዝተ አለም ስላሴ ፣ዲዎስቆሮስ
8.
ኪሮስ ፣ማቲዮስ፣ ኪሩቤል አርባእቱ እንስሳ፡ ዘካርያስ
9.
ሰልስቱ ምዕት፣ ቶማስ ፣እስትንፋሰ ክርስቶስ ፣አትናትዮስ
10.
መስቀለ ክርስቶስ ፣ናትናኤል ሐዋርያ ፣ፀደንያ ማርያም
11.
ሐና እና ኢያቄም ፣አቡነ ሐራ
12.
ሚካኤል፣ አባ ሳሙኤልና ናትናኤል ሐዋርያ
13.
ፀጋ ኢየሱስ/ ዘርአ ብሩክ/ ፣ሩፋኤል ፣እግዚአብሔር አብ
14.
አቡነ አረጋዊ ፣ገብረ ክርስቶስ/ገብረ መርአዊ/ ዘሚካኤል ፣ሙሴ ፀሊም
15.
ቂርቆስና እየሉጣ ፣ሚናስ
16.
ኪዳነ ምህረት ፣ኤልሳቤጥ
17.
እስጢፋኖስ ፣ገሪማ ፣ወለተ ጴጥሮስ ፣አቡነ በትረ ማርያም ያዕቆብ ወልደ ዘብዲዮስ ፣ሙሴ
18.
ማዕቀብ አልፋ ፣ኢዩስጣቲዮስ ፣ፊሊጶስ
19.
ገብርኤል ፣ስልስቱ ደቂቅ፣ ይመርሐነ ክርስቶስ
20.
፣ዮሐንስ ሀፂር ፤ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን
21.
ቅድስት ድንግል ማርያም
22.
ሉቃስ ፣ደቅስዮስ ፣ኡራኤል ብስራተ ገብርኤል
23.
ቅዱስ ማር ጊዮርጊስ
24.
ተክለ ሐይማኖት ፣ጎርጎርዮስ 24 ካህናተ ሰማይ፣ ክርስረቶስ ሰምራ
25.
ቅዱስ መርቆሬዎስ ፣አቡነ ሀቢብ
26.
ዮሴፍ፣ ቶማስ ዘህንደኬ፣ አቡነ ሀብተ ማርያም
27.
መድሐኔአለም ፣አቡነ መባዓ ፅዮን ተክለ አልፋማርያም
28.
አማኑኤል .አበው አብርሃም ይህሳቅ ያዕቆብ
29.
በዓለ እግዚአብሔር (በዓለወልድ)፣ቅዱስ ላሊበላ ፣ቅድስት አርሴማ
30.
ቅዱስ ማርቆስ ዮሐንስ መጥምቅ
እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።ዘሌ 192 በተባለው መሰረት ቅዱስ የሚለው ስያሜ በምግባር በቱርፋትለጽኑ የሚታየውን አለም ለለወጡ ከዚህ አለም ደስታ ተድላ ይልቅ ዘላለማዊውን ለመረጡ ፤በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ እራሳቸውን ለኃላፊው ነገር ላላስገዙ የሚሰጥ ስያሜ ነው። ስለዚህመ ለቅዱሳን የሚገባውን መታሰቢያ እናደርጋለንእንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና። እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ። /ዕብ 1126/ የተባለው በፅናትና በትጋት እግዚአብሔርን ላገለገሉ ቅዱሳን ነው፡፡