Thursday, April 30, 2020

ዜና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን መንግስት በመስቀል አደባባይና ጃንሜዳ እያከናወነ ያለው ተግባር መብቴን ጥሷል አለች
++++++++++++
ዋዜማ ራዲዮ- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀትና የመስቀል ዳመራ የሚከበሩበት መስቀል አደባባይና ጃንሜዳ ላይ መንግስት ፈቃደኝቴን ሳይጠይቅ ሳያማክረኝ በወሰዳቸው እርምጃዎች “የባለቤትነት” መብቴን ተጋፍቷል ለዚህም ማብራሪያ እንዲሰጠኝ ስትል ጠየቀች።
ለዋዜማ ራዲዮ የደረሰው ከቤተ ክርስቲያኒቱ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የተላከው ደብዳቤም ይህንኑ ይገልጻል።
በአቡነ ያሬድ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚለው እነዚህ ከመንፈሳዊና ባህላዊ እሴቶች በተጨማሪ ለሀገሪቱ ትልቅ የገቢ ምንጭ በመሆን የታወቁትን በአላት ማክበሪያ ቦታዎችን የበለጠ በመንከባከብና እሴቶቻቸውን በመጠበቅ የቱሪስት ፍሰቱ እንዲጨምርና የሀገሪቱ ገቢ አድጎ የህዝቡን ተጠቃሚነት በበለጠ ሁኔታ እንዲረጋገጥ ለቦታዎቹ ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ በማድረግ ፈንታ ይባስ ብሎ የበአለ ጥምቀቱን ቦታ ለገበያ ማእከልነት እንዲሁም የበአለ መስቀል ማክበሪያውን ቦታ ደግሞ “ምንነቱ ላልታወቀ” ፕሮጀክት እንዲውል ሲያደርግ የበአሉም ሆነ የቦታው ጥንተ ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያኒቱ ሳትጠየቅና በጉዳዩ ላይ ሳታምንበት ግልፅነት በጎደለው ሁኔታ ወደ ትግበራ በመገባቱ ቤተ ክርስቲያኒቱን በእጅጉ ያሳዘነ ተግባር ነው።
እንዲሁም በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታና ቁጣን በማስከተሉ የመልካም አስተዳደር ችግር እየፈጠረብን ነውም ይላል ደብዳቤው። ደብዳቤው አክሎም የከንቲባ ጽህፈት ቤት የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት በማስገባትና ልዩ ትኩረት በመስጠት በጉዳዩ ላይ ተገቢውም አፋጣኝ ምላሽ ይስጠን ሲል ይጠይቃል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ያግዘኛል በሚል ፒያሳ ያለውን የአትክልት ተራ መጨናነቅ ለመቀነስ ገበያውን ወደ ጃንሜዳ መቀየሩ ይታወቃል። ከቀናት በፊት ደግሞ አዲስ አበባን የማስዋብ እቅድ አካል ነው የተባለ የመስቀል አደባባይ ማዘጋጃ ቤት ፕሮጀክትን ለመስራት የመስቀል አደባባይን መቆፈር ተጀምሯል።የዋዜማ ሪፖርተር ስፍራው ላይ ተገኝቶ እንደተመለከተው የቁፋሮው ስራ እጅጉን እየተፋጠነ ነው።
በቤተክርስቲያኒቱ ለጉዳዩ ከፍተኛ ቅርበት ያላቸው ግለሰብ ከዋዜማ ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ መንግስት በፈጸመው ድርጊት የቤተ ክርስቲያኒቷን ህጋዊ መብት ተጋፍቷል ብለውናል። የጃን ሜዳውን እና የመስቀል አደባባዩ ጉዳይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ስጋት መፍጠሩን ያነሳሉ። የጃን ሜዳውን የአትክልት ግብይት ቦታ መሆኑን በተመለከተ ፣ መንግስት ይህን ያደረገው የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ነው መባሉ በራሱ ችግር ባይሆንም ፣ እንደተባለው ጃን ሜዳ ለገበያ ቦታነት የተፈለገው በጊዜያዊነትና የወረርሽኙ ጊዜ እስኪያልፍ ለመሆኑ ምን ማረጋጫ አለ ? የሚል ጥያቄ በቤተ ክርስቲያኒቱ ዘንድ አለ ይላሉ። አሁን ጊዜያዊ ተብሎ ቀጣይ የሚኖር አስተዳደር ቦታውን በቋነሚት ወደ ግብይት ቦታ ልቀይር አለማለቱ በምን ይታወቃል? ይህም በቀጣይ ግጭትና አላስፈላጊ ንትርክ ሊያስከትል ስለሚችል ከተማ አስተዳደሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሳያማክርና አስተያየቷን ሳይቀበል : ይሁንታንም ሳያገኝ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰበትን ህጋዊ መሰረት እንዲያስረዳም ነው ቤተ ክርስቲያን የምትፈልገው ብለውናል ምንጫችን።
የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ቅሬታ እንደገባትም ጠቁመውናል። የመስቀል በአል በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ላይ ሲሰፍር ያለው አረደዳድ የተመዘገበው በዓሉም ብቻ ሳይሆን የዳመራ ስነስርአቱና የሚከበርበት ቦታ እንደመሆኑ ታዲያ የአዲስ አባበ ከተማ አስተዳደር የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክትን አስመልክቶ ይፋ ያደረገው በቪድዮ የተደገፈ ዲዛይን ለቤተ ክርስቲያኒቱ እንግዳ ነገር ሆኖባታልም ።
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት ግለሰብ እንዳሉን በቪድዮ የተደገፈው ዲዛይን ደመራው የሚተከልበትን ቦታ እና የተለያዩ መንፈሳዊ ትርኢቶች የሚታዩባቸው ስፍራዎች ላይ ዛፍ ተተክሎበት ስለሚያሳይ የመስቀል ደመራ እንዴት እንዲከበር ታስቦ ዲዛይኑ እንደተሰራም ግራ አጋቢ በመሆኑ ለቤተ ክርሰቲያኗ ማብራሪያ አስፈጓታል።

ጻድቁ ተክለሃይማኖት በጸሎት እግሩ እንደተሰበረች በቅኔ


መነነቶ ወኅደገቶ
ለተክለሃይማኖት አብ ጽኑዓ ሃይማኖት መሐላ
ብእሲት እግሩ ዘዓቢይ ኅይላ
ወኢፈቀደት ነቢረ ውሳጤ ቀዊም መርጡላ
ስድስተ አክናፈ ደቂቀ ተድላ
በላዕሌየ ወለደ ብሂላ
#ትርጉም: ሃይሏ ትልቅ የሆነ እግሩ/ሴት የሀይማኖት መሃላን ያጠና ተክለሃይማኖትን ናቀችውና ተወችው። ስድስት ክንፎችን/የምቾት ልጆችንም በላዬ ወለደ ብላ በመቆሚያ ቤቷ ውስጥ መኖርን አልወደደችም።
#ትንታኔ፡ የጎልማሳ ሚስት ባልዋ በላይዋ ላይ ከሌላ ሴት ልጅ ከወለደ ትታው እንደምትለየው ሁሉ ጻድቅ ተክለሃይማኖትም ሰባት ዓመት ቆመው  ሲጸልዩ አንድ እግራቸው ተሰብሮ ስድስት የጸጋ ክንፎች አገኙ ይላሉ ባለቅኔው።
ባለቅኔው መሪጌታ ያሬድ ዘቂርቆስ

Wednesday, April 29, 2020

ምክረ አበው


"በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው"ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ
"ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል" ቅዱስ ቆጵሮሳዊ
"የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው" ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ
"መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም" ቅዱስ ባስልዮስ
"ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር" ሊቁ ጠርጡለስ

Monday, April 27, 2020

ቃለ እግዚአብሔር

++ እንዴት ወድቀን እንዴት ተነሣን? ++
እንዴት ወድቀን እንዴት ተነሳን በዲ.ን ሔኖክ ኃይሌ
ኦሪት ዘፍጥረት ስለሰው ልጅ ውድቀት ሲናገር ዕባብና ሔዋን ያደረጉትን ቃለ ምልልስና በዕባብ ምክር ሠጪነት የሰው ልጅ እንዴት ከገነት እንደተባረረና ጸጋውን እንደተገፈፈ ያስረዳል፡፡

    ይህንን የዕባብና የሔዋን ቃለ ምልልስን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብናወጣው ወይም ኦሪት ዘፍጥረት የአዳምና ሔዋንን ከገነት መባረር ብቻ የሚናገር ቢሆን ኖሮ ‹ምን አጥፍተው ነው የተባረሩት?› ወደሚል ግራ መጋባት ውስጥ እንገባ ነበር፡፡

    ወዳጄ የዕባብና ሔዋንን ቃለ ምልልስ መስማት ሳይችል  የአዳምና ሔዋንን ከገነት የመባረር ታሪክ ለመረዳት የሚችል እንደሌለ ሁሉ የእመቤታችንንና የቅዱስ ገብርኤልን ቃለ ምልልስ ሳያነብ የሰው ልጅን ወደ ገነት የመግባትና የመዳን ታሪክ ለመረዳት የሚችል ሰው ማንም የለም፡፡

 
ቅዱስ ጳውሎስ በአዳምና በክርስቶስ ተምሳሌት (Christ-Adam analogy) አድርጎ ጻፈ::  ክርስቶስን ‹ኋለኛው አዳም› ብሎ ጠርቶታል፡፡ (1ቆሮ. 15፡45) አዳምንም ‹አዳም ይመጣ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነው› በማለት የክርስቶስ ምሳሌ እንደሆነ አስረድቷል፡፡ (ሮሜ. 5፡14) የሰው ልጅ ተፈጥሮ ታሪክ የተጀመረው ከአዳም ታሪክ እንደነበር የሰው ልጅ አዲሱ ተፈጥሮ ታሪክም የተጀመረው በዳግም ፍጥረት (Recaptulation) በተፈጠርንባት በቀራንዮ ነው፡፡

ይህም ንጽጽርም  በኁዋላ ዘመን ለተነሡ እንደሰማዕቱ ዮስጦስና እንደ ያዕቆብ ዘሥሩግ ያሉ ሊቃውንት የማርያምና ሔዋን ተምሳሌትን (Mary eve analogy) እንዲያመሠጥሩ መነሻ ሆናቸው:: ያነጻጸሩት ሔዋንን ከማርያም ብቻ ሳይሆን እንዴት ወደቅን እንዴት ተነሣን የሚለውን ነው::

ሔዋን ለውድቀታችን መነሻ ነበረች ማርያም ግን ለመነሳታችን ምክንያት ሆነች:: ሔዋንን ሰይጣን በዕባብ ተመስሎ አነጋገራት:: ማርያምን ግን እግዚአብሔር በገብርኤል ሆኖ አነጋገራት:: ሔዋን የዕባቡን ቃል በመስማትዋ ከገነት ወጣን : ማርያም የገብርኤልን ቃል በመስማትዋ ወደ ገነት መለሰችን::

የዕባብና የሔዋንን ቃለ ምልልስ በቁጭት እናነበዋለን:: የድንግልና የገብርኤልን ምልልስ ግን በደስታ እንጸልየዋለን:: ያ ቃለ ምልልስ እኛን ወደ ሕይወት የመለሰ ቃለ ምልልስ ነው:: የ15 ዓመትዋ ብላቴና ማርያም ምድራዊያንን ሁሉ ወክላ ከሰማያዊው መልእክተኛ ጋር ተነጋግራ ዕርቃናችንን አለበሰችን:: የድሆች ልጅ የሆነችው ብላቴና የመላእክትን አለቃ በጥያቄ አስጨንቃ መርምራ ከጭንቃችን ገላገለችን::

ሔዋን የዕባብን ምክር ሳትመረምር ተቀበለች:: ድንግል ማርያም ግን የገብርኤልን ብሥራት መረመረች:: ለሔዋን ዲያቢሎስ "እግዚእብሔር እንደርሱ እንዳትሆኑ ብሎ ከለለላችሁ" ብሎ ከፈጣሪ አጣላቸው:: ሔዋን ሁሉን አዋቂ ለመሆን ቸኩላ ከባልዋ ጋር ፈጠነች:: ድንግል ማርያም ግን ሁሉን አዋቂ ልሁን አላለችም :: "ወንድ ስለማላውቅ እንዴት ይሆንልኛል? ብላ ጠየቀች : ሔዋን አምላክ ለመሆን ተታለለች:: ትሕትና የሞላባት ድንግል ግን "እነሆኝ የጌታ ባሪያው ነኝ" ብላ ተቀበለች::

ይህች ድንግል ገብርኤልን ሰምታ የሕይወትን ዛፍ አበላችን:: ይህች ድንግል ይሁንልኝ በማለትዋ የተጠመቅን ሁላችን ክርስቶስን ለበስን:: በእርስዋ ይሁንልኝ ማለት ኪሩብ ሰይፉን ጣለ : ከጥበቃም ተገላገለ:: እኛም ከዕፀ ሕይወት እንበላ ዘንድ ታደልን::

ብዙ ሰው " ሔዋን ለመውደቃችን ምክንያት ናት " ሲባል ይስማማል:: ድንግል ማርያም ግን ለመዳናችን ምክንያት ሆነች የሚለውን ግን አንዳንዶች ለመቀበል ይቸገራሉ:: ሔዋን ለመውደቃችን ካደረገችው ይልቅ ድንግል ማርያም ለመነሣታችን ያደረገችው ይበልጣል!

የድኅነታችን መጀመሪያ የሆነችውን ይህችን ድንግል ክብርዋን በሕሊናችን እንሳለው:: እሳታዊ መልአክ ቆሞ የዘመረላት ድንግል : አባትዋ ዳዊት ከሩቅ ሆኖ እያያት "ልጄ ሆይ ስሚ እዪም ጆሮሽን እዘንብዪ" እያለ የገብርኤልን ቃል እንድትሰማና ከሲኦል እንድታወጣው የሚማጸናትን ድንግል : ወንድምዋ ሰሎሞን "እኅቴ ሙሽራ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም" እያለ የቀረበላትን 'የተባረክሽ ነሽ' የሚል ምስጋና እንድትቀበል የሚዘምርላትን :  በእጆችዋ ሐርና ወርቅን : በማኅጸንዋ ሰውና አምላክን : በመውለድዋ ሰውና መላእክትን አስማምታ የፈተለችና ያዋሐደችዋን ይህች ድንግል እስቲ ለአፍታ እናስባት:: የባቢሎንን ሰባት እጥፍ የነደደ እሳት ያቀዘቀዘው ገብርኤል በፊትዋ በትሕትና አደግድጎ የቆመላትና ዘካርያስን ዲዳ ትሆናለህ ባለበት አንደበቱ "አንቺ የተባረክሽ ነሽ " እያለ የሚማጸናትን የዐሥራ አምስት ዓመት ብላቴና እስቲ እናስባት! ዓላማ ይዞ እንደተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ይህች ማናት?

ሽማግሌ አባትዋን ቅጠል ከለበሰበት ዛፍ አውጥታ ልጅዋን ሸማ አድርጋ ያለበሰች : እናትዋን ሔዋንንም የሚጎዳ ማሠሪያዋን ፈትታ ቁስልዋን ያከመች የሔዋን መድኃኒት ይህች ድንግል ማን ናት? የእርስዋን ክብር በኃጢአተኛ ብዕር እንደምን እጽፈዋለሁ?
ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ያለውን ብዬ ብዘጋው ይሻለኛል
"የድንግል ማርያምን ክብር ከመግለጽ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 21 2012
አዲስ አበባ

Sunday, April 26, 2020

ፎቶ ጋለሪ

ይዘጋጃል…

ቅዱስ ያሬድ

ኢትየጵያዊዉ ቅዱስ ያሬድ ሚያዝያ 5 ቀን 505 ዓ/ም በአክሱም ከተማ ተወለደ፡፡እናቱ ታዉክሊያ/ክርስቲና/አባቱ ደግሞ ይስሐቅ/አብድዩ/ይባላሉ፡፡አባቱ የ አክሱም ጽዮን ቄሰ ገበዝ ነበር፡፡

በዓላት

በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።ኢሳ.56:5
የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው።ምሳ 107 እግዚአብሄር ለቅዱሳን በቸርነቱ ከሰጣቸው በረከት ለመሳተፍ መታሰቢያቸውን ማድረግ የግድ ነውእናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።”/ማቴ 1040-46/ ይላልና ይህም የተባለው በነብያት፣ በጻድቃንና በሌሎችም ቅዱሳን ስም መታሰቢያ ማድረግ እንደሚገባ ለመግለጽ ነው።እንደሚገባት በዓላትን እና ንዑስ በዓላትን ሙሉ በሙሉ ሳናካትት በከፊል ዓመታዊ በዓላትን እና ወርሃዊ በዓላትን ስንክሳር እና ገድላትን በማንበብ በጦማራችን አቅርበንሎታል፡፡ ለወደፊትም ስራቸውን በተቻለ እናቀርባለን::ዓመታዊ በዓላት
መስከረም 1. ቅዱስ ራጉኤል (ርእስ አውደ ዓመት/
መስከረም 2. ቅዱስ ዮሀንስ /አንገቱ የተቆረጠበት ቀን/
መስከረም 10. ፀደኒያ ማርያም
መስከረም 15 ቅዱስ እስጢፋኖስ(የተሾመበት) (ይህ በዓል ከመስቀል በዓል ጋር የሚታሰብ ነው)
መስከረም 17 ቅዱስ እስጢፋኖስ /በዓለ መስቀል/
መስከረም 21. መናገሻ ማርያም ፡ግሼን ማርያም ፡እንጦጦ ማርያም
መስከረም 29. ቅድስት አርሴማ
ጥቅምት 5. አቡነ ገብረመንፈስ
ጥቅምት 9. አባ አትናስዮስ(እረፍቱ)
ጥቅምት 12.አባ ዲሜጥሮስ(እረፍቱ)
ጥቅምት 13.አባ ዘካርያስ(እረፍቱ)
ጥቅምት 14. አቡነ አረጋዊ (የተሰወሩበት) በገብረክርስቶስ(እረፍቱ) ኢትዮጰያዊውን ጀንደረባ ያጠመቀውን ዲያቆኑ ፊሊጶስ (እረፍቱ)
ጥቅምት 17. ቅዱስ እስጢፋኖስ(የተሸመበት)
ጥቅምት 20. ዮሐንስ ሐፂር(እረፍቱ)
ጥቅምት 21.ነቢየ እግዚአብሔር ኢዩኤል (እረፍቱ)
ጥቅምት 22. ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ (እረፍቱ) ጥቅምት 25 አቡነ ሀቢብ አረፈ
ጥቅምት 27. መድሐኔአለም: አባ መብዓ ፅዮን (እረፍታቸው)
2
ጥቅምት 8. ቅዱስ አማኑኤል
ጥቅምት 30. ቅዱስ ማርቆስ /ልደቱ/
ህዳር 6. ቁስቋም ማርያም እመቤታችን ስደቷን ጨርሳ የገባችበት
ህዳር 7. ሕንጻ ቤቱ ለጊዮርጊስ/ አጥንቱ ተሰብስቦ መቃብር ቤት የገባበት/
ህዳር 8. በዓል አርባዕቱ እንስሳ /ክሩቤል ሱራፌል/አባኪሮስ
ህዳር 11. ዕረፍተ ቅድስት ሀና
ህዳር 12. ቅዱስ ሚካኤል፡
ህዳር 13. እግዚአብሔር አብ/የአእላፍ መላእክት ቀን
ህዳር 14. አባ ዳንኤል እረፍቱ
ህዳር 15. ቅዱስ ሚናስ እረፍቱ
ህዳር 18. ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ እረፍቱ 12 ሐዋርያት አንዱ
ህዳር 21. ፅዮን ማርያም/የእመቤታችን በዓል/
ህዳር 24. ሀያአራቱ ካህናተ ሰማይ /ደብረ ሊባኖስ/
ህዳር 25. ቅዱስ መርቆሪዎስ ሰማዕቱ /እረፍቱ/
ህዳር 26. አቡነ ሀብተማርያም /ደብረሊባኖስ/ አባ ኢየሱስ ሞአ(እረፍቱ)
ህዳር 27. አባ ተክለሃዋርያት ሐዋርው ቅዱስ ያዕቆብ በሰማዕትነት አረፈ
ህዳር 29. ተፈፃሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ(እረፍቱ)
ታህሳስ 1.ነቢዩ ኤልያስ የተወለደበት ቀን
ታህሳስ 3. በአታ ለማርያም እመቤታችን በሶስት አመቷ ቤተመቅደስ የገባችበት፡ አቡነ ዜና ማርቂስ(እረፍቱ)
ታህሳስ 4. ሐዋርያው እንድርያስ በሰማዕትነት ያረፈበት
ታህሳስ 6. ቅድስት አርሴማ(ቅዳሴ ቤቷ)
ታህሳስ 12. አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
ታህሳስ 13. ቅዱስ ሩፋኤል
ታህሳስ 15. አባ ጎርጎርዮስ (እረፍቱ) ዘሀገረ አርማንያ
ታህሳስ 19. በዓለ ቅዱስ ገብርኤል
ታህሳስ 22. ብስራተ ገብርኤል /እመቤታችን ክርስቶስን እንደምትወልድ ያበሰረበት/
ታህሳስ 24. አቡነ ተክለሀይማኖት /ልደታቸው/
ታህሳስ 28. ቅዱስ አማኑኤል በዓለ ልደት ለእግዚእነ ገና
ታህሳስ 29. ቅዱስ በዓለ ወለድ /ተዘከረ ልደቱ ለእግዚነ/ገና/
ጥር 1. ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሚ ሰማእት (እረፍቱ)
ጥር 4. ቅዱስ ዮሐንስ /ወንጌላዊ/ወልደ ነጎድጓድ
ጥር 6. ኢየሱስ/ግዝረቱ ለእግዚእነ /እየሱስ ገዳም/ ነቢዩ ኤልያስ የተሰወረበት ቀን
ጥር 7. ቅድስት ሥላሴ
ጥር 11. በዓለ ጥምቀት
ጥር 12. በዓለ ቅዱስ ሚካኤል /ቃና ዘገሊላ/
ጥር 13. ቅዱስ ሩፋኤል /የቃና ዘገሊላ በዓል መታሰብያ/
ጥር 14 አቡነ አረጋዊ
ጥር 15. ቅዱስ ቂርቆስ እየሉጣ
ጥር 18. ቅዱስ ጊዮርጊስ /ዝርዎተ አጽሙ/
ጥር 21. የእመቤታችን በዓለ እረፍት
ጥር 22. ቅዱስ ኡራኤል ቃል ኪዳን የተቀበለበትና የተሸመበት ቀን
ጥር 23. ሐዋርያው ጢሞቲዋስ (እረፍቱ)
ጥር 24. አቡነ ተክለሃይማኖት
ጥር 28. ቅዱስ አማኑኤል 5000 ሰዎች ጌታችን ህብስቱን ያበረከተበት
 
የካቲት 3. አባ ያዕቆብ (እረፍቱ)
የካቲት 8. ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ወደ ምኩራብ የገባበት ቀን(የአረጋዊው የስምዖን ታሪክ ልብ የበሉ)
የካቲት 9. አባ በርሱማ (እረፍቱ)
የካቲት 15. ነቢዩ ዘካርያስ (እረፍቱ)
የካቲት 16. ኪዳነምህረት /እመቤታችን ቃልኪዳን የተቀበለችበት/
የካቲት 20. ቅዱስ ፊልጶስ
የካቲት 23. ቅዱስ ጊዮርጊስ
የካቲት 26. ነቢዩ ሆሴዕ (እረፍቱ)
የካቲት 28. ሮማዊው ቅዱስ ቴዌድሮስ(እረፍቱ)
መጋቢት 4. ቅዱስ ጊዮርጊስ /ደብረዘይት/
መጋቢት 3. ተዝካረ ልደቱ ለአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
መጋቢት 10. መስቀሉን ንግስት እሌኒ ቆፍሬ ያገኘችበት ቀን መድሀኔአለም
መጋቢት 15. ቅድስት ሳራ(እረፍቷ)
መጋቢት 22. ጥንተ ሆሳእና
መጋቢት 27. ቸሩ መድሃኒአለም (የጌታችን ጥንተ ስቅለቱ መታሰቢያ)
መጋቢት 29. የበዓለ ወልድ /የጌታችን ጽንሰት/
ሚያዝያ 22. አባ ይስሀቅ(እረፍቱ)
ሚያዝያ 23. የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ እረፍት
ሚያዝያ 27. ምስካየ ሕዙናን /ስደተኛው መድሀኒአለም/
ሚያዝያ 30. ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ያረፈበት ቀን ነው
ግንቦት 1. ልደታ እመቤታችን የተወለደችበት ቀን ነው
ግንቦት 7. ሊቁ አቡነ አትናቲዎስ (እረፍቱ)
ግንቦት 11. ቅዱስ ያሬድ(የተሰወረበት)
ግንቦት 12. አቡነ ተክለሃይማኖት /አፅማቸው የፈለሰበት /ክርስቶስ ሳምራ
ግንቦት 14. አቡነ አረጋዊ፡ ቅዱስ ገብረክርስቶስ
ግንቦት 17. አባ ኤጲፋንዮስ(እረፍቱ)
ግንቦት 21 . እመቤታችን ማርያም /እመቤታችን
ግንቦት 24. ቁስቋም ማርያም /የስደቷ መነሻ/
ግንቦት 28. ቅዱስ አማኑኤል፡ ቅድስት አመተ ክርስቶስ (እረፍቷ)
ሰኔ 8. ከደረቅ ዓለት ላይ ውሃን ያፈለቀበት 33 ከእመቤታችን በዓል አንዱ
ሰኔ 9. ታላቁ ነብይ ሳሙኤል(እረፍቱ)(የሐና ልጅ)
ሰኔ 11.ሰማዕቱ ቅዱስ ገላውድዮስ (እረፍቱ)
ሰኔ 12. ቅዱስ ሚካኤል ባሕራንን ከውሃ ያወጣበት ቀን ነው(አፎምያን ከሰይጣን ያዳነበት) ቅዱስ ላሊበላ(እረፍቱ)
ሰኔ 20.ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን
ሰኔ 21. ጌታችን /የእመቤታችንን ቤት ያነጸበት ቀን ነው፡፡ ግሽን ማርያም በጎልጎታ በጌታችን መቃብር የጸለየችበት
ሰኔ 23.ጠቢቡ ሰሎሞን እረፍቱ
ሰኔ 24. አባ ሙሴ ፀሊም(እረፍቱ)
ሰኔ 25. የዮሴፍ ልጅ ሐዋርው ይሁዳ እረፍቱ
ሰኔ 26. ኢያሱ እረፍቱ
ሰኔ 27. እረፍቱ ለሐናንያ ሐዋርያ
ሰኔ 30. ልደተ ዮሐንስ መጥምቅ
ሐምሌ 2. ሐዋርያው ታዴዎስ(እረፍቱ)
ሐምሌ 3. አባ ቄርሎስ(እረፍቱ)
ሐምሌ 4. ነቢዩ ሶፎንያስ እረፍቱ
ሐምሌ 5. ጴጥሮስና ጳውሎስ እረፍታቸው
ሐምሌ 7. አጋእዝተ ዓለም ስላሴ በአብርሃም ቤት፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እረፍቱ
ሐምሌ 8. አባ ኪሮስ
ሐምሌ 10.ሓዋርያው ናትናኤል እረፍቱ
ሐምሌ 15. ኤፍሬም ሶርያዊው እረፍቱ
ሐምሌ 16. ወንጌላዊው ዮሐንስ እረፍቱ
ሐምሌ 18 .የጻድቁ የዮሴፍ ልጅ ሐዋርያው ያዕቆብ እረፍቱ
ሐምሌ 19. በዓለ ቅዱስ ገብርኤል ቂርቆስና እየሉጣን ከእሳት ያዳነበት ቀን ነው/ቁልቢ ገብርኤል/
ሐምሌ 22. ቅዱስ ኡራኤል ፡አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት የተቀበሉበት
ሐምሌ 23. ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሐምሌ 26. ቅዱስ ዮሴፍ (እረፍቱ) ፡አቡነ ሀብተማርያም ዘደብረሊባኖስ
ሐምሌ 28.ቅድስት መስቀል ክብራ (እረፍቷ)(የቅዱስ ላሊበላ የትዳሩ አጋር)
ሐምሌ 30.ቅድስት ማርያም ክብራ(እረፍቷ)
ነሐሴ 7.ፅንሰታ ለማርያም
ነሐሴ 13. እግዚአብሔር አብ በደብረታቦር ተራራ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱ ለእነ ሙሴና ኤልያስ የገለጸበት ቀን ነው/የቡሄ በዓል/
ነሐሴ 15. ቅድስት እነባመሪና(እረፍቷ)
ነሐሴ 16. ኪዳነምህረት
ነሐሴ 19. አባ መቃርስ የስጋው ፈልሰት
ነሐሴ 21. ጌቴ ሴማኒ ገዳም እመቤታችን (ሰበታ)
ነሐሴ 24. አቡነ ተክለሃይማት እረፍታቸው ፤ክርስቶስ ሳምረ
ነሐሴ 27 ቅዱስ ሱርያል(4 ሊቀ መላእክት)
ነሐሴ 28.አበው አብርሃም ይህሳቅ ያዕቆብ (እረፍታቸው)
ጳጉሜ 2.ሐዋርያው ቲቶ (እረፍቱ)
ጳጉሜ 3. ቅዱስ ሩፋኤል
ጳጉሜ 4.አባ ባይሞን(እረፍቱ)
ወርሃዊ በዓላት
1.
ልደታ፣ዮሐንስ ፣ራጉኤል ፣እዮብ ፣ኤልያስ ሶስና
2.
በርቶሎሚዎስ ፣ጴጥሮስ ፣አባ ጉባ ፣መሪና
3.
በአታ ማርያም ፣ፋኑኤል ፣ዜና ማርቆስ
4.
ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ፣አባ መቃርዎስ፣ አባ አብርሐ
5.
ጴጥሮስና ጳውሎስ ፣ገብረ መንፈስ ቅዱስ
6.
ቁስቋም ፣ኢየሱስ ፣አርሴማ ቅድስት ፣እያሱ
7.
አጋዕዝተ አለም ስላሴ ፣ዲዎስቆሮስ
8.
ኪሮስ ፣ማቲዮስ፣ ኪሩቤል አርባእቱ እንስሳ፡ ዘካርያስ
9.
ሰልስቱ ምዕት፣ ቶማስ ፣እስትንፋሰ ክርስቶስ ፣አትናትዮስ
10.
መስቀለ ክርስቶስ ፣ናትናኤል ሐዋርያ ፣ፀደንያ ማርያም
11.
ሐና እና ኢያቄም ፣አቡነ ሐራ
12.
ሚካኤል፣ አባ ሳሙኤልና ናትናኤል ሐዋርያ
13.
ፀጋ ኢየሱስ/ ዘርአ ብሩክ/ ፣ሩፋኤል ፣እግዚአብሔር አብ
14.
አቡነ አረጋዊ ፣ገብረ ክርስቶስ/ገብረ መርአዊ/ ዘሚካኤል ፣ሙሴ ፀሊም
15.
ቂርቆስና እየሉጣ ፣ሚናስ
16.
ኪዳነ ምህረት ፣ኤልሳቤጥ
17.
እስጢፋኖስ ፣ገሪማ ፣ወለተ ጴጥሮስ ፣አቡነ በትረ ማርያም ያዕቆብ ወልደ ዘብዲዮስ ፣ሙሴ
18.
ማዕቀብ አልፋ ፣ኢዩስጣቲዮስ ፣ፊሊጶስ
19.
ገብርኤል ፣ስልስቱ ደቂቅ፣ ይመርሐነ ክርስቶስ
20.
፣ዮሐንስ ሀፂር ፤ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን
21.
ቅድስት ድንግል ማርያም
22.
ሉቃስ ፣ደቅስዮስ ፣ኡራኤል ብስራተ ገብርኤል
23.
ቅዱስ ማር ጊዮርጊስ
24.
ተክለ ሐይማኖት ፣ጎርጎርዮስ 24 ካህናተ ሰማይ፣ ክርስረቶስ ሰምራ
25.
ቅዱስ መርቆሬዎስ ፣አቡነ ሀቢብ
26.
ዮሴፍ፣ ቶማስ ዘህንደኬ፣ አቡነ ሀብተ ማርያም
27.
መድሐኔአለም ፣አቡነ መባዓ ፅዮን ተክለ አልፋማርያም
28.
አማኑኤል .አበው አብርሃም ይህሳቅ ያዕቆብ
29.
በዓለ እግዚአብሔር (በዓለወልድ)፣ቅዱስ ላሊበላ ፣ቅድስት አርሴማ
30.
ቅዱስ ማርቆስ ዮሐንስ መጥምቅ
እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።ዘሌ 192 በተባለው መሰረት ቅዱስ የሚለው ስያሜ በምግባር በቱርፋትለጽኑ የሚታየውን አለም ለለወጡ ከዚህ አለም ደስታ ተድላ ይልቅ ዘላለማዊውን ለመረጡ ፤በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ እራሳቸውን ለኃላፊው ነገር ላላስገዙ የሚሰጥ ስያሜ ነው። ስለዚህመ ለቅዱሳን የሚገባውን መታሰቢያ እናደርጋለንእንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና። እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ። /ዕብ 1126/ የተባለው በፅናትና በትጋት እግዚአብሔርን ላገለገሉ ቅዱሳን ነው፡፡