Pages

Pages

Thursday, April 30, 2020

ዜና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን መንግስት በመስቀል አደባባይና ጃንሜዳ እያከናወነ ያለው ተግባር መብቴን ጥሷል አለች
++++++++++++
ዋዜማ ራዲዮ- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀትና የመስቀል ዳመራ የሚከበሩበት መስቀል አደባባይና ጃንሜዳ ላይ መንግስት ፈቃደኝቴን ሳይጠይቅ ሳያማክረኝ በወሰዳቸው እርምጃዎች “የባለቤትነት” መብቴን ተጋፍቷል ለዚህም ማብራሪያ እንዲሰጠኝ ስትል ጠየቀች።
ለዋዜማ ራዲዮ የደረሰው ከቤተ ክርስቲያኒቱ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የተላከው ደብዳቤም ይህንኑ ይገልጻል።
በአቡነ ያሬድ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚለው እነዚህ ከመንፈሳዊና ባህላዊ እሴቶች በተጨማሪ ለሀገሪቱ ትልቅ የገቢ ምንጭ በመሆን የታወቁትን በአላት ማክበሪያ ቦታዎችን የበለጠ በመንከባከብና እሴቶቻቸውን በመጠበቅ የቱሪስት ፍሰቱ እንዲጨምርና የሀገሪቱ ገቢ አድጎ የህዝቡን ተጠቃሚነት በበለጠ ሁኔታ እንዲረጋገጥ ለቦታዎቹ ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ በማድረግ ፈንታ ይባስ ብሎ የበአለ ጥምቀቱን ቦታ ለገበያ ማእከልነት እንዲሁም የበአለ መስቀል ማክበሪያውን ቦታ ደግሞ “ምንነቱ ላልታወቀ” ፕሮጀክት እንዲውል ሲያደርግ የበአሉም ሆነ የቦታው ጥንተ ባለቤት የሆነችው ቤተ ክርስቲያኒቱ ሳትጠየቅና በጉዳዩ ላይ ሳታምንበት ግልፅነት በጎደለው ሁኔታ ወደ ትግበራ በመገባቱ ቤተ ክርስቲያኒቱን በእጅጉ ያሳዘነ ተግባር ነው።
እንዲሁም በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታና ቁጣን በማስከተሉ የመልካም አስተዳደር ችግር እየፈጠረብን ነውም ይላል ደብዳቤው። ደብዳቤው አክሎም የከንቲባ ጽህፈት ቤት የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት በማስገባትና ልዩ ትኩረት በመስጠት በጉዳዩ ላይ ተገቢውም አፋጣኝ ምላሽ ይስጠን ሲል ይጠይቃል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ያግዘኛል በሚል ፒያሳ ያለውን የአትክልት ተራ መጨናነቅ ለመቀነስ ገበያውን ወደ ጃንሜዳ መቀየሩ ይታወቃል። ከቀናት በፊት ደግሞ አዲስ አበባን የማስዋብ እቅድ አካል ነው የተባለ የመስቀል አደባባይ ማዘጋጃ ቤት ፕሮጀክትን ለመስራት የመስቀል አደባባይን መቆፈር ተጀምሯል።የዋዜማ ሪፖርተር ስፍራው ላይ ተገኝቶ እንደተመለከተው የቁፋሮው ስራ እጅጉን እየተፋጠነ ነው።
በቤተክርስቲያኒቱ ለጉዳዩ ከፍተኛ ቅርበት ያላቸው ግለሰብ ከዋዜማ ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ መንግስት በፈጸመው ድርጊት የቤተ ክርስቲያኒቷን ህጋዊ መብት ተጋፍቷል ብለውናል። የጃን ሜዳውን እና የመስቀል አደባባዩ ጉዳይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ስጋት መፍጠሩን ያነሳሉ። የጃን ሜዳውን የአትክልት ግብይት ቦታ መሆኑን በተመለከተ ፣ መንግስት ይህን ያደረገው የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ነው መባሉ በራሱ ችግር ባይሆንም ፣ እንደተባለው ጃን ሜዳ ለገበያ ቦታነት የተፈለገው በጊዜያዊነትና የወረርሽኙ ጊዜ እስኪያልፍ ለመሆኑ ምን ማረጋጫ አለ ? የሚል ጥያቄ በቤተ ክርስቲያኒቱ ዘንድ አለ ይላሉ። አሁን ጊዜያዊ ተብሎ ቀጣይ የሚኖር አስተዳደር ቦታውን በቋነሚት ወደ ግብይት ቦታ ልቀይር አለማለቱ በምን ይታወቃል? ይህም በቀጣይ ግጭትና አላስፈላጊ ንትርክ ሊያስከትል ስለሚችል ከተማ አስተዳደሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሳያማክርና አስተያየቷን ሳይቀበል : ይሁንታንም ሳያገኝ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰበትን ህጋዊ መሰረት እንዲያስረዳም ነው ቤተ ክርስቲያን የምትፈልገው ብለውናል ምንጫችን።
የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ቅሬታ እንደገባትም ጠቁመውናል። የመስቀል በአል በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ላይ ሲሰፍር ያለው አረደዳድ የተመዘገበው በዓሉም ብቻ ሳይሆን የዳመራ ስነስርአቱና የሚከበርበት ቦታ እንደመሆኑ ታዲያ የአዲስ አባበ ከተማ አስተዳደር የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክትን አስመልክቶ ይፋ ያደረገው በቪድዮ የተደገፈ ዲዛይን ለቤተ ክርስቲያኒቱ እንግዳ ነገር ሆኖባታልም ።
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት ግለሰብ እንዳሉን በቪድዮ የተደገፈው ዲዛይን ደመራው የሚተከልበትን ቦታ እና የተለያዩ መንፈሳዊ ትርኢቶች የሚታዩባቸው ስፍራዎች ላይ ዛፍ ተተክሎበት ስለሚያሳይ የመስቀል ደመራ እንዴት እንዲከበር ታስቦ ዲዛይኑ እንደተሰራም ግራ አጋቢ በመሆኑ ለቤተ ክርሰቲያኗ ማብራሪያ አስፈጓታል።

ጻድቁ ተክለሃይማኖት በጸሎት እግሩ እንደተሰበረች በቅኔ


መነነቶ ወኅደገቶ
ለተክለሃይማኖት አብ ጽኑዓ ሃይማኖት መሐላ
ብእሲት እግሩ ዘዓቢይ ኅይላ
ወኢፈቀደት ነቢረ ውሳጤ ቀዊም መርጡላ
ስድስተ አክናፈ ደቂቀ ተድላ
በላዕሌየ ወለደ ብሂላ
#ትርጉም: ሃይሏ ትልቅ የሆነ እግሩ/ሴት የሀይማኖት መሃላን ያጠና ተክለሃይማኖትን ናቀችውና ተወችው። ስድስት ክንፎችን/የምቾት ልጆችንም በላዬ ወለደ ብላ በመቆሚያ ቤቷ ውስጥ መኖርን አልወደደችም።
#ትንታኔ፡ የጎልማሳ ሚስት ባልዋ በላይዋ ላይ ከሌላ ሴት ልጅ ከወለደ ትታው እንደምትለየው ሁሉ ጻድቅ ተክለሃይማኖትም ሰባት ዓመት ቆመው  ሲጸልዩ አንድ እግራቸው ተሰብሮ ስድስት የጸጋ ክንፎች አገኙ ይላሉ ባለቅኔው።
ባለቅኔው መሪጌታ ያሬድ ዘቂርቆስ